You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

#Prosperityparty
ስለ ሰላም ሀያልነት አያሌ ጊዜ ተነግሯል፤ በርግጥም የሰላም መስፈን ጥቅሙ ሆነ የጋራችን እንደሆነ ሁሉ ሰላም ማጣታችንም ጉዳቱ ለሁላችንም መሆኑ ግልጽ ነው፡፡


የህግ የበላይነት መከበርና የዴሞክራሲ መጎልበት ለኛ ለዜጎች የሚኖራቸው ጠቀሜታ ቀላል አይደለም፤ በመሆኑም ሰላማችን እንዳይደፈርስ፣ ብዝሃነትን ያከበረ ዴሞክራሲያዊ አብሮነታችን እንዲጎለብት ስንል አንድነታችን የሚፈታተኑ ሃይሎች የሚፈፀሙትን እኩይ ተግባራት መመከት፣ ማጋለጥና ማክሸፍ ብሎም እንደ ሀገር የጀመርነውን ሀገራዊ ለውጥ አጠናክረን በመቀጠል የሰላም ዘብ መሆናችን በተግባር ልናሳይ ይገባል፡፡


አንድነት ሀይል ነው ሲባል ሰምተን ይሆናል፡፡ በርግጥም ልክ ነው የእኛ አንድ መሆን ኢትዮጵያን ለሚጠሉ የውስጥና የውጭ ሀይሎች ሁነኛ መድሐኒት ነው፡፡በአንድነት የማንወጣው ዳገት እና ተራራ አይኖርም፡፡


ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያን ከውስጥና ከውጭ ወራሪ እና እንደ ትህነግ ያሉ ከሃዲ ተንኳሽ ሀይሎችን አይቀጡ ቅጣት አድርሰን ወራሪዎችን ወደ መጡበት የመለስናቸው እንዲሁም ተንኳሱን የትህነግ ቡድን ከእኩይ ሴራው አደብ ያስገዛነው መላው ኢትዮጵያዊያን ባሳየነው አንድነት እንደሆነ ለማንም የተደበቀ አይደለም፡፡

ምላሽ ይስጡ