You are currently viewing የብልጽግና ፓርቲ እና የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ግንኙነታቸው በሚጠናከርበት ጉዳይ መከሩ

የብልጽግና ፓርቲ እና የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ግንኙነታቸው በሚጠናከርበት ጉዳይ መከሩ

  • Post comments:0 Comments

#Prosperityparty

የሁለቱ ፓርቲዎች አመራሮች በቀጣይ የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቱን አጠናክረው ስለሚቀጥሉበት ጉዳይ በዌብናር ውይይት አካሄደዋል፡፡

ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የተለያዩ ስኬታማ ልምዶች ያለው ፓርቲ እንደሆነ ገልጸው፤ የብልጽግና ፓርቲ የጀመረውን ሁለንተናዊ ሪፎርም ለማጠናከርና ውጤታማ ለማድረግ ከቻይና ፓርቲ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ቢቂላ ኢትዮጵያ የህግ ማስከበር ስራ ላይ እንደነበረችና የህግ ማስከበሩ እንደተጠናቀቀ ለቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አመራሮች ገልጸዋል፡፡ በትግራይ ክልል የነበረው የህግ ማስከበር ስራ በመጠናቀቁ የትግራይ ህዝብ ወደ ሰላማዊ የእለት ከእለት እንቅስቃሴው የተመለሰ ሲሆን በአገራችን በ2013 ዓ.ም ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ በብልጽግና ፓርቲ በኩል እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶችን አስረድተዋል፡፡

በውይይቱ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ተገኝተው የኢትዮጵያና የቻይናን ቆየት ያለ ወዳጅነት አብራርተዋል፡፡ አምባሳደሩ ኢትዮጵያና ቻይና ስትራቴጅካዊ ወዳጆች እንደሆኑ ገልጽው አገሪቱ በብዙ ዘርፍ እንደተጠቀመች ነው የገለጹት፡፡

ሁለቱ አገራት በአሁኑ ወቅት በበርካታ ጉዳዮች ላይ አብረው እየሰሩ እንደሚገኙ የገለጹት አምባሳደሩ በቻይና የኮቪድ ወረርሽኝ የተከሰተ ሰሞን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለፕሬዝዳንት ዥ ጅፒንግ ስልክ በመደወልና ኢትዮጵያ ከቻይና ጎን እንደሆነች በመግለጽ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ነበሩ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን በወከል በውይይቱ የተገኙት የአፍሪካ ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክተር ሚስተር ዋንግ ሂሚንግ የብልጽግናና የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል የፓርቲያችን ፍላጎት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ በተለይም ከምስራቅ አፍርካ አገራት ጋር ለምናደርገው ግንኙነት ኢትዮጵያን እንደማእከል እንደሚጠቀሙ ለዚህም ኢትዮጵያን እየመራት ከሚገኘው የብልጽግና ፓርቲ ጋር ጠንካራ ግንኙነት መመስረት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ፍላጎት ነው ብለዋል፡፡

ቻይና በየትኛውም አገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ፍላጎት እንደሌላት የገለጹት ሚስተር ዋንግ ሂሚንግ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮቿን በራሷ የመምራትና ህግና ስርዓት የማስፈን መብት ያላት አገር መሆኗን አብራርተዋል፡፡

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ብልጽግና ፓርቲ ለሚያካሂዳቸው የፓርቲ ሪፎርም ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጾል፡፡የብልጽግናና የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ግንኙነታቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ያስችላቸው ዘንድ በቅርቡ የመግባቢያ ሰነድ ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምላሽ ይስጡ