You are currently viewing የህወሃት ቡድን የሕልውናው መሰረት በብሔረሰቦች መካከል ክፍፍልና ግጭት መፍጠር ነበር:- የሱማሌ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ

የህወሃት ቡድን የሕልውናው መሰረት በብሔረሰቦች መካከል ክፍፍልና ግጭት መፍጠር ነበር:- የሱማሌ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ

  • Post comments:0 Comments

የህወሃት ቡድን የሕልውናው መሰረት በብሔረሰቦች መካከል ክፍፍልና ግጭት መፍጠር እንደነበር የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ገልጸዋል፡፡የህወሃት ቡድን በተለያዩ ክልሎች ግጭት እንዲነሳ ሲያደርግ እንደነበር የሱማሌ ክልል አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ገልጸዋል፡፡

ቡድኑ በተለይ የኦሮሞና የአማራ ብሔረሰቦች መካከል ልዩነት እንዲኖር ቡድኑ በዋናነት ሲሰራ እነደነበርም አቶ ሙስጠፌ ተናግረዋል፡፡የሱማሌና የኦሮሞ ግጭትም የዚህ የህወሃት ተግባር አካል ነው ብለዋል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ቡድኑ በሌሎች ክልሎች ግጭት እንዲባባስ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግና ትግራይ ክልል ውስጥ ግጭትን እንዲኖር የሚያደርግ አካል ባለመኖሩ ትግራይ ሰላማዊ ሆኖ እንዲታይ በማድረግ የ27 ዓመት የስልጣን ዘመኑ በአገሪቱ ከመጣው ሪፎርም የተሻለ መሆኑን ለማሳየት ጥረት ሲያደርግ ነበር ብለዋል አቶ ሙስጠፌ፡፡

አቶ ሙስጠፌ፣ የሕወሃት ቡድን ለ27 በዓመታት በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የፈጸመው ወንጀል ይቅርና በቅርቡ በማይካድራ የፈጸመው ወንጀል ብቻ እንደ ዓለም አቀፍ ሽብርተኛ እንዲፈረጅ ሊያደርገው ይችላል ብለዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ