በትግራይ ክልል ከቀዬአቸው ሸሽተው የነበሩ ዜጎች መመለስ ጀመሩ

በትግራይ ክልል ከቀዬአቸው ሸሽተው የነበሩ ዜጎች መመለስ ጀመሩ

  • Post comments:0 Comments

በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ከቀዬአቸው ሸሽተው የነበሩ ዜጎች መመለስ መጀመራቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
ቤታቸውን ጥለው ሊሸሹ የቻሉት የትህነግ ታጣቂ ቡድን መከላከያ ሊያጠፋችሁ ነው የሚል የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛቱ ነው ተብሏል።
ወ/ሮ ናፍታሃ ገ/ስላሴ በትግራይ ክልል፣ ህንጣሎ ዋጅራት ወረዳ፣ ጸሀፍት ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በቅርቡ ቤታቸውን ጥለው በመሸሽ ለአንድ ሳምንት ያህል በዱር መቆየታቸውን ይናገራሉ። አሁን ግን በአካባቢው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተሰማርቶ ሰላም በመስፈኑ ወደቀዬአቸው መመለስ ችለዋል።
በህንጣሎ ዋጅራት ወረዳ ከተማ በንግድ ስራ የሚተዳደሩት አቶ ካህሳይ ሰመሮም በተመሳሳይ ከአካባቢያቸው ሸሽተው በዱር በመቆየታቸው የተለያዩ ችግሮች እንደገጠሟቸው ገልጸው አሁን ግን በከተማዋ የእለት እለት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ ወደከተማዋ ተመልሰው የንግድ ስራቸውን መጀመራቸውን ተናግረዋል።
የጽንፈኛው ትህነግ ታጣቂዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሊያጠፋችሁ ነው ብለው ሀሰተኛ መረጃ ስለሰጡን ቤታችንን በመተው ወደ ዱር እንድንሰደድ ተገደን ነበር ያሉት ነዋሪዎቹ ስለ መከላከያ ሠራዊቱ የተነገረን ፈጽሞ ሀሰት መሆኑን በተግባር አረጋግጠናል ብለዋል።
አሁንም ከቀዬአቸው ርቀው ያሉ ሌሎች ዜጎች እንዲመለሱ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን እየሰሩ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

Leave a Reply