የህዝብ ግንኝነት ስራ ማጠናከርና የሚዲያ አጠቃቀም የምክክር መድረክ ተካሄደ

የህዝብ ግንኝነት ስራ ማጠናከርና የሚዲያ አጠቃቀም የምክክር መድረክ ተካሄደ

  • Post comments:0 Comments

በሶማሊ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፀ/ቤት የተዘጋጀ ይህ የምክክር መድረክ የክልሉ ቢሮ ሀላፊዎች እና የህዝብ ግንኝነት ባለሞያዎች ተሳትፎበታል።

የመድረኩ መክፈቻ ስነስርዓት ላይ የመድረኩ ዓላማን በተመለከተ ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንሰ ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ በደል እንደተናገሩት ለውጡን ተከትሎ ቢሮው በሰላምና ዲሞክራሲ ዙሪያ ከሚዲያዎችና ህዝብ ግንኝነት ጋር እየተደረገ ያለው የመረጃ ቅብብሎሽ ለማጠናከርና፤ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ከማድረግ ጋር ተያይዞ ይበልጥ የተጠናከረና ወጥ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር የክልሉ ቢሮ ሀላፊዎች ከባለሞያዎች ጋር እየተናበቡ እንዲሰሩ እንዲሁም ለህዝብ ግንኝነት ስራ ትኩረት እንዲሰጡበት የአቅም ግንባታ ጋር ተያይዞ ግንዛቤ ለመፍጠር የምክክር መድረክ አሰፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ መሀመድ ሻሌ በበኩላቸው በክልሉ የሚገኙት የተለያዩ የህዝብ ግንኝነት ባለሞያዎች በኩል የተሰሩ ስራዎችን በማድነቅ የህዝብ ግንኝነት ስራ ግቡን እንዲመታ በየሴክተሩ ያሉ የስራ ሀላፊዎች ተናቦ እንዲሰሩ በመገለፅ ባለሞያዎችም የሀገር ሰላም ግንባታ ግቡን እንዲመታ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥረ አቅርቧል።

የክልሉ ኮምኒውኬሽን ጉዳዬች ምክትል ቢሮ ሃላፊ ሂቦ በመንግሥት የተከናወኑ ያሉ መሰረተ ልማቶችን በተመለከተም ለመሀበረሰብ ከማሳወቅ ጀምሮ ጠንካራ የመንግሥትና የህዝብ ግንኙነትን ለመፍጠር የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ለሚመለከታቸው አካላቶች በተለያዩ ግዜዎች መስጠት መቻሉንም ተናግረዋል።

ከመንግስት ከፍተኛ የስራ አመራሮችና ከህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎች ጋርም በዛሬው እለት የተካሄደው የውይይት መድረክ ከክልሉ የኮምኒኬሽን ጉዳዬች ቢሮ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ተስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ነው የገለፁት።

በስልጠናው ላይ የስራ ሀላፊዎች ጨምሮ የህዝብ ግንኝነትና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ሲሆን በኮሙኒኬሽን ስራዎችና በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ እንዲሁም የህዝብ ግንኝነት በዘርፉ ልምድ ባላቸው ተጋባዥ ባለሙያዎች የስልጠና ሰነዶች ቀርበዋል።

በቀረቡ ሰነዶቹ ላይ ዉይይት ከተደረገበት በኋላ በቀጣይ የስራ ሀላፊዎችና የህዝብ ግንኝነት ባለሞያዎች የክልሉ ኮሚዩኒኬሽንሰ ጉዳዮች ቢሮ ሊያሻሺላቸዉና ሊያጠናክራቸዉ በሚገባቸው ነጥቦች ላይ አሰተያየት በመሰንዘር ተጠናቀዋል።

Leave a Reply