የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ አካሄዱ

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ አካሄዱ

  • Post comments:0 Comments

“ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን ” በሚል መሪ ቃል የህወሓት አጥፊ ቡድን የፈጸመውን የክህደት ተግባር በማውገዝና ለመከላከያ ሰራዊታችን ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ አካሂደዋል

በደም ልገሳው ተሳታፊ የነበሩ የጽ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች መከላከያ ሰራዊት አገርና ህዝብን ለመጠበቅ ህይወቱን ሳይሰስት መስዋዕት እያደረገ ያለ በመሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ መሳተፋቸው ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት ያለቸውን ክብር የገለጹበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ የተፈፀመው የሴረኞች ጥቃት እጅግ እንዳሳዘናቸውና ህይወቱን ለህዝብ እና ለሀገሩ አሳልፎ ለመስጠት ለማይሳሳው የአገር መከላከያ ሰራዊት ደም መስጠት ቢያንስ እንጂ እንደማይበዛ የመርሀ ግብሩ ተሳፊዎች አክለው ገልፀዋል፡፡

ጁንታው ቡድን የመጨረሻ ምእራፍ ላይ በሚገኝበት እየተደረገ ያለው የህግ ማስከበር ስርአት እጅግ ስኬታማ እየሆነ ባለበት በዚህ ወቅት የደም ልገሳ መርሀ ግብር ማካሄዳቸው ለሰራዊቱ ተጨማሪ ጉልበት እንደሚሆን እምነት አለን ብለዋል፡፡

የህወሃት ጁንታ ቡድን ላይ የተጀመረው ህግን የማስከበር ዘመቻን በድል እየተወጣ ለሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ ከዚህ በኋላም አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን በማድረግ ያላቸውን አጋርነት እንደሚያሳዩ ተናግረዋል፡፡የደም ልገሳ መርሃ ግብሩን የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አስተባብሮታል፡፡

Leave a Reply