You are currently viewing ኢ ት ዮ ጵ ያ  በቅርብ ቀን ከጫፍ ጫፍ  የሰላም አየር ይነፍስባታል፤ ህዝቦቿ በነጻነት የትም ሄደው  መኖር ይጀምራሉ

ኢ ት ዮ ጵ ያ በቅርብ ቀን ከጫፍ ጫፍ የሰላም አየር ይነፍስባታል፤ ህዝቦቿ በነጻነት የትም ሄደው መኖር ይጀምራሉ

  • Post comments:1 Comment

ሰራዊታችን በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የተጣለበትን ህዝባዊ አደራና በክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተሰጠው ትዕዛዝ  መሰረት በመቀሌ የመሸገውን ዘራፊውን የህወኃት ቡድን ለህግ የማቅረብና ህግ የማስከበር ስራ በውጤታማነት እንደሚፈጽመው ጥርጥር የለውም፡፡

ሰሜናዊቷ ኮከብ መቀሌ የኢትዮጵያዊያን መዳረሻ ከተማ ናት፤ሁሉም የሚናፍቃት የታታሪ ህዝቦች ምደር፡፡ስለሆነም እየተወሰደ ያለው ህግን የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ግቡን ይመታ ዘንድ በከተማዋ የምትኖሩ ነዋሪዎች በሚወሰደው እርምጃ አላስፈላጊ መስዋዕት እንዳትከፍሉ በቤታችሁ በመቀመጥ እንዲሁም በጁንታው የህወኃት ቡድን ነፍጥ ያነገባችሁ ትጥቃችሁን ፈታችሁ ለህግ የበላይነት መከበር ባለቤት እንድትሆኑና ታሪካዊ ሀላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል፡፡

የሆነው ሆኖ  በጀግናው ሰራዊታችን የቆዬ ልምድ፣ጥበብ የተሞላበት አካሄድ፣ብስለት የታከለበት ጥቃት፣ወታደራዊ ኢላማዎችን በመመረጥ የመሸገውን ጁንታው የህወኃት ቡድንን ለህግ በማቅረብ ፍርድ እንዲያገኙ መደረጉ አይቀሬ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በቅርብ ቀን ከጫፍ ጫፍ የሰላም አየር ይነፍስባታል፤ህዝቦቿ በነጻነት የትም ሄደው መኖር ይጀምራሉ፡፡የቆየው አንድነታችን ይመለሳል፤ የወንድማማችነት እሴታችን ጎልብቶ ከኢትዮጵያ አልፎ ለዓለም ያበራል፡፡

This Post Has One Comment

ምላሽ ይስጡ