You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

አሸባሪነት የህወኃት ምስለኔነት

በሚራክል እውነቱ

የትግራይ ህዝብ ለሀገረ መንግስት ምስረታ ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን ያበረከተው አስተዋጾኦ ጉልህ ነው፡፡ ህዝቡ የጎለበተ፣ ጠንካራ ታሪካዊ ትስስር ያለው፣ ሰላም ፈላጊ፣ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ የሚተጋ ብሎም ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር ተዋህዶ የኖረና የሚኖር ህዝብ ነው፡፡

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ከሃዲው የህወኃት አጥፊ ቡድን ለዘመናት ከብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተቻችሎ፣ ተዋልዶና ተዛምዶ የኖረን የትግራይ ህዝብ በተንኮልና በሴራ ለመለያየት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም፡፡ በዚህም ሳያበቃ ፅንፈኛው የህወኃት ቡድን የትግራይን ህዝብ እንደ ምሽግ በመቁጠር ዛሬም ድረስ ሽንፈቱን ከመቀበል ይልቅ ፉከራ ማሰማቱን ቀጥሏል፡፡

በወለጋ፣ በጉራፈርዳ፣ በመተከል፣ በኮንሶና በማይካድራ ለጠፋው የንጹሃን ሞት፣ መፈናቀልና የእርስ በእርስ ግጭት ዋናው መሐንዲሱ ህዝብ አንቅሮ የተፋው ዘራፊው ህወኃት ቡድን መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህ አጥፊ ቡድን ማንነትን መሰረት ያደረገ እልቂት በመፍጠር በታሪክ ተከትቦ የሚቀመጥ ጥቁር ጠባሳ በህዝብ ዘንድ አሳርፏል፡፡

አይ ኤስ አይ ኤስ በሊቢያ በርካታ ኢትዮጵያዊያን አንገታቸውን በመቅላት ሲገድል እናቶች ወገባቸውን አደግድገው እንባ ተራጭተዋል፡፡ የሰው ልጅ ስለምን ይሄን ያህል በሰው ላይ ይጨክናል ሲሉ ለፈጣሪያቸው አልቅሰዋል፤አውግዘዋል፡፡ ዛሬ ይህ ሽብር በአገራችን በህወሓት አጥፊ ቡድን ተፈጽሟል፡፡ ሰዎች በማንነታቸው ብቻ ያለርህራሄ ተረሽነዋል፡፡ ይህ ቡድን በዓለም ላይ በአሸባሪነታቸው ከተፈረጁ ቡድኖች የላቀውን በደል በራሱ ህዝብ ላይ ፈጽሟል፡፡ አሸባሪው የአልሸባብ ቡድን በምስራቅ አፍሪካ በርሃማ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ህዝብን በጅምላ ጨረሰ፣ አቆሰለ፣ አፈናቀለ፤ ጽንፈኛው የህወኃት ቡድንም በተመሳሳይ መልኩ በማይካድራ ለዘመናት ተሳስሮ የኖረን ህዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ረሸናቸው፡፡

በናይጄሪያ የሚንቀሳቀሰው ቦኮሃራም ህዝብ የሚበዛባቸውን ስፍራዎች በመለየት፣ ህጻናት በብዛት የሚጫወቱበትን ቦታ በመምረጥ፣ በተሽከርካሪዎች እና በተለያዩ ፌስታሎች ወይም እቃዎች ቦንብና ፈንጂዎችን በማስቀመጥ የበርካታ ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል፤ እዚሁ ሀገራችን የሚገኘው ጁንታው የህወኃት ቡድንም በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞችን በመምረጥ ለአዛውንቶች ሳይሳሳ፣ ለህፃናት ሳይራራ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸመ፡፡  እና ህወሓት ለንጹሃን ከማይሳሳው ከአሸባሪው አልሸባብ በምን ተለየ?

መንግስት ይሄንን አገራችንን ያረከሰውን ኢትዮጵያዊነትን የመረዘውን እኩይ ቡድን ላይ ነው እርምጃ እየወሰደ ያለው፡፡ በመሆኑም በትግራይ ክልል ያላችሁ ሀገር ወዳድ ህዝቦች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተሰጠውን የ72 ሰዓታት ዕድሜ ሊጠናቀቅ ሰዓታት ብቻ እንደቀሩት አስባችሁ በጁንታው የህወኃት ቡድን ላይ እየተደረገ ያለውን ህግ የማስከበር እርምጃ አጋዥ በመሆን ታሪካዊ ሀላፊነታችሁን መወጣት ይገባችኋል፡፡ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ያላችሁ ወንድማዊና ቤተሰባዊ ግንኙነታችሁ ላይ ሳይቋረጥ የትግራይን ህዝብ የሚያለያዩ ሙከራዎችን በፅናት እንድትታገሉና ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለማስቀጠል በሚደረገው ትግል ውስጥ ጉልህ ሚናችሁን ልትወጡ ይገባል፡፡

ድል ለሰራዊታችን !

ምላሽ ይስጡ