You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

አገራችን ውስጥ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከህወሃት አጥፊ ቡድንና በጥምረት ከሚንቀሳቀሱት ኦነግ ሸኔና ካደራጇቸው የጥፋት ኃይሎች ውጭ የአገራችንን ሰላም ለማወክ የሚራወጥ ኃይል እንደሌለ ግልጽ ነው። ባለፉት ዓመታት ከባዕዳን ጋር ሳይቀር በማበር አገር ለመውጋት ሲያሴሩ የነበሩት እነዚህ ሃይሎች አሁንም ብዙሃኑ የአገራችን ህዝብ ሰላሙ እንዲመለስት ዘወትር የሚተጋውን ያህል የጥፋት ቡድኖቹ የየእለት ተግባራቸው በሰውና በንብረት ላይ ጥፋት ማድረስ መሆኑን እየተመለከትን ነው።

ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ መዲናችን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገራችን ክልሎች ለጥፋት የተከዘኑ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የአገራችን ህዝብ አካባቢውን ከአጥፊዎች ለመጠበቅ ያሳየው ቁርጠኝነትም ለማድረስ የታሰበውን ጥፋት ማክሸፍ ችሏል። መንግስት ዓላማው ግልጽ ነው፡፡ አገራችን የጥቂቶች መፈንጫ የምትሆንበት እድል መዝጋት፡፡

ከዚህ ባሻገር ለዓመታት ግፍ የደረሰበትን ህዝብ በቁርጠኝነት በመካስና የአገር ክህድት የፈጸሙትን ኃይሎች የሚገባቸውን ቅጣት በመስጠት ወደመዳረሻችን መገስገስ ላይ ማተኮር ነው የመንግስት ዓላማ፡፡ በመሆኑም በእኔ ብቻ ልጠቀም አባዜ አቅሉን የሳተውንና ለአንድነታችንና ለመተሳሰባችን ሳንካ ሆኖ የቆየውን ሴረኛ የጥፋት ቡድን ከህዝብ ጫንቃ ላይ በማስወገድ አገራችን ሁሉም ዜጋ በእኩልነትና ነጻነት የሚኖርባት አገር ለማድረግ በጀመርነው የትብብር መንፈስ ወደፊት መገስገሳችን ይቀጥላል፡፡

ምላሽ ይስጡ