You are currently viewing የ22ኛ ክፍለ ጦር አባላት ለታላቁ ህዳሴ ግድብና ለአካባቢው ደህንነት መረጋገጥ ተገቢውን ጥበቃ እያደረጉ እንደሚገኙ አስታወቁ

የ22ኛ ክፍለ ጦር አባላት ለታላቁ ህዳሴ ግድብና ለአካባቢው ደህንነት መረጋገጥ ተገቢውን ጥበቃ እያደረጉ እንደሚገኙ አስታወቁ

  • Post comments:0 Comments

በአገር መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ እዝ 22ኛ ንስር ክፍለ ጦር አባላት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንደወትሮው በትጋት እየሰሩ መሆኑን ተናገሩ።ከክፍለ ጦሩ አባላት መካከል ሌተናል ኮሎኔል ወንድሙ ሃብቴ እንደገለጹት፤ የ22ኛ ንስር ክፍለ ጦር አባላት አብዛኞቹ ለ21 ዓመታት በትግራይ ክልል የህዝብ ደጀን በመሆን አገልግለዋል።“ሠራዊቱ የትግራይ ህዝብን ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ ሌት ተቀን በደሙ፣ በጉልበቱ፣ በገንዘቡ እና አቅሙ በቀፈቀደ ሁሉ መስዋዕትነት ከፍሏል” ብለዋል፡፡ጽንፈኛና ከሀዲው የህወሃት ቡድን በሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ያደረሰው ግፍ የተሞላበት ጭፍጨፋ ለሠራዊቱ ፈጽሞ የማይመጥን፣ አረመኒያዊ እና የሚወገዝ ድርጊት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡የአብዛኛው የሰሜን ዕዝ ክፍለ ጦር አባላት በቅርቡ ለተጨማሪ ሃገራዊ ግዳጅ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እንደተዛወሩ ገልጸው፤ ለህዝብ ክብር የተሰዉ ጓዶቻቸውን በማሰብ በቁጭት እየሠሩ መሆኑን ሌተናል ከሎኔል ወንድሙ አስረድተዋል፡፡“በሃገራችን ሠላም ሲያሳጣ የኖረውን የህወሃት ጁንታ ለህግ እንዲቀርብ የጀመርነውን ዘመቻ በስኬት እንወጣለን” ያሉት ደግሞ የክፍለ ጦሩ አባል ምክትል አስር አለቃ ገነት ቢቂላ ናቸው፡፡የትግራይ ህዝብ የጁንታውን ህወሃት አባላት አጋልጦ በመስጠት ለሠራዊቱ ያለውን አጋርነት እንዲያሳይም ጠይቀዋል።የህዳሴው ግድብ ከፍጻሜ እስኪደርስ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገልጸው፤ “በፕሮጀክቱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሚነሳ የትኛውንም ሃይል አንታገስም” ብላለች።“የሰሜን ዕዝ አባሎቻችን መስዋዕትነት የፈጠረብን ቁጭት ተጨማሪ ወኔ እና ጉልበት ሆኖናል” ያለው ሻምበል ሄኖክ ተክለማርያም፤ የጁንታው ተላላኪዎች በመተከል ዞን የግድቡን አካባቢ ለማወክ የሚያደርጉትን ጥረት ለማክሸፍ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጿል።“ተላላኪዎችን ለህግ ለማቅረብ ሌት ከቀን እየሰራን ነው” ሲል አስረድቷል፡፡“ህዝባችን የሠጠን ህገ-መንግስቱን የመጠበቅ ሃላፊነት በመወጣት ሀገራችንን የማስከበር ተልዕኳችንን እናሳካለን” ብሏል ሻምበል ሄኖክ፡፡በምዕራብ ዕዝ የ22ኛ ንስር ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ነገሪ ቶሊና “ህብረተሰቡ ለሠራዊቱ ያሳየው ክብር ለበለጠ ሃላፊነት አነሳስቶናል” ብለዋል፡፡ “በሠራዊቱ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ውስጣዊ አንድነታችንን ለማፈራረስ በተነሱ ቡድኖች የተጠነሰሰ ሴራ ነው” ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ነገሪ፤ ሠራዊቱ ህዝባዊ ወገንተኝትን ያነገበ በመሆኑ ሴራው መክሸፉን ገልጸዋል፡፡“የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ህዝብ ህልውና እንደሆነ ገልጸው፤ “ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን ከምንጊዜውም በላይ ለዓለም አጉልቶ ያሳየ ነው” ብለዋል፡፡ በጁንታው ተልዕኮ በህዳሴ ግድብ አካባቢው ሁከት ለመፍጠር የሚደረግ ተደጋጋሚ ሙከራ እንዳለ የሚገልጹት አዛዡ፤ ከውስጥም ሆነ ከውጪ ሊቃጡ ለሚችሉ ማናቸውም የጥፋት ድርጊቶች አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ሰራዊቱ በተጠንቀቅ ላይ እንደሆነ ገልጸዋል።

ምላሽ ይስጡ