You are currently viewing የህወሓት ጁንታ ቡድን ከህዝብ ጫንቃ የሚወገድበት ወሳኝ ምዕራፍ!

የህወሓት ጁንታ ቡድን ከህዝብ ጫንቃ የሚወገድበት ወሳኝ ምዕራፍ!

  • Post comments:0 Comments

/ከዮሐና ማርካን/ የትግራይ ክልል ህዝብን ከህወሓት የጥፋት ቡድን በማላቀቅ ለዓመታት ተነፍጎ የቆየውን የዴሞክራሲና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ይበል የሚያሰኝ ተግባር ነው፡፡ የህወሓት ጁንታ ቡድን ትናንት የህዝብ ሃብት ሲመዘብር ጉዳዩ ያላለውን ብዙሃኑን የትግራይን ህዝብ ዛሬ ወንጀል ሰርቶ መሸሸጊያው አድርጎታል፡፡ ከህወሓት ውጭ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በነጻነት እንዳይንቀሳቀሱ ጫና ከማድረግ ባለፈ ለእስርና እንግልት ጭምር በመዳረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሳንካ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ዛሬ ግን የትግራይ ህዝብ የይስሙላ ሳይሆን እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚያይበት፣ በኃይል ሳይሆን በፍላጎት ድጋፉንም ተቃውሞውን የሚገልጽበት ጊዜ ተቃርቧል፡፡ በትግራይ ህዝብ ስም እየማሉና እየተገዘቱ ለህዝቡ አንዳች ጠብ የሚል ነገር ሳያበረክቱ ዓመታትን የህዝብ ሃብት ሲመዘብሩ የኖሩ የጥፋት ቡድኖች የመጥፊያቸው የመጨረሻ ቀን ላይ ይገኛሉ፡፡ የዚህ አምባገነነ ቡድን መወገድ ለትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የአገራችን ህዝብ የድል ዜና እንደሚሆን እሙን ነው፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በማህበራዊ ሚዲያ ገጹ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክር ቤት በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አካሂዷል የሚል ዜና አስነብቧል። ዜናው በእርግጥም የትግራይ ህዝብ አሁን የሚያስፈልገው በተባበረ ክንድ ይሄንን የጥፍት ቡድን አስወግዶ ክልሉን ሰላማዊ ወደሆነ ሁኔታና የልማት እንቅስቃሴ የሚያስገባው ኃይል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ የላቀ ሚና አላቸው፡፡የህወሓት አጥፊ ቡድን ወትሮም ለህዝብ ቆምኩኝ ይበል እንጂ ከፕሮፓጋንዳ የዘለለ ተግባር ሲከውን እንዳልነበር የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡ በመሆኑም በቀጣይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክር ቤት እንደገለፀው የአስተዳደር መዋቅር ማስተካከል፣ የክልሉ ሰላም እና ደኅንነት ማስጠበቅ እና ማረጋገጥ፣ ፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ማስጠበቅ እና ማረጋገጥ፣ የተቋረጠውን ማኅበራዊ አገልግሎት ማስቀጠል፣ የክልሉን ኢኮኖሚ እንዲያገገም ማድረግ እንዲሁም በቀጣይ ከሚካሄደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በክልሉ ውስጥ መንቀሳቀስ ለሚፈልጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሐሳባቸውን በነፃነት አቅርበው እንዲወዳደሩ የፖለቲካ ምህዳሩን ማመቻቸት ሥራዎች ላይ በህብረት እና በአንድነት በመስራት ህዝብን እያወናበዱ መኖር ፈጽሞ እንደማይቻል ለጁንታው ግልጽ መልዕክት ማስተላለፍ ያስፈልጋል፡፡ አሁንም አላማው አንድ እና አንድ ነው፡፡ አምባገነንነትን፣ ከፋፋይነትን፣ ትዕቢትንና በህዝብ ላብ መክበርን ቀብሮ ሰላማዊ የሆነችና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሳይሸማቀቀ የሚኖርባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ፡፡ ይህ ደግሞ አገር በማተራመስ ህዝብን እረፍት የነሳውን ጁንታ አርቆ በመቅበር እውን ይሆናል፡፡

ምላሽ ይስጡ