ሠሞኑን በድባጤ ወረዳ ቂዶህ ቀበሌ በንጹኃን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከሰብዓዊነትም ሆነ ከኢትዮጵያዊነት ውጪ የሆነ የወንጀለኞች የክፋት ጠርዝ እና የጭካኔ ጥግ ማሳያ እኩይ ተግባር ነው- የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ

ሠሞኑን በድባጤ ወረዳ ቂዶህ ቀበሌ በንጹኃን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከሰብዓዊነትም ሆነ ከኢትዮጵያዊነት ውጪ የሆነ የወንጀለኞች የክፋት ጠርዝ እና የጭካኔ ጥግ ማሳያ እኩይ ተግባር ነው- የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ

  • Post comments:0 Comments

ሠሞኑን በድባጤ ወረዳ ቂዶህ ቀበሌ በንጹኃን ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከሰብዓዊነትም ሆነ ከኢትዮጵያዊነት ውጪ የሆነ የወንጀለኞች እኩይ ተግባር የክፋቱን ጠርዝ እና የጭካኔውን ጥግ የሚያሳይ ፍጹም ሠይጣናዊ የሆነ እኩይ ተግባር መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽና ፓርቲ ጽ/ቤት ገለጸ፡፡ፓርቲው በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ በጣዕረ-ሞት ውስጥ የሚገኘው የህወሓት ጁንታ ቡድን ቀደም ሲል በአምሳሉ የቀረፃቸውና የጥፋት ተልዕኮ ሰጥቶ ያሰማራቸው ቅጅዎቹ በክልላችን እየፈፀሙ ያሉትን የሽብር ተግባር ለማስቆም በጋራ ልንረባረብ ይገባል ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡የመግለጫው ሙሉ ሃሳብ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡በሸፍጥ፣ በክህደት እና በሴራ ፖለቲካ ጥርሱን ነቅሎ ያደገው ፣ ዘራፊውና ጨፍጫፊው የህወሃት ወንበዴ ቡድን ላለፉት ዓመታት ክልላችንን ጨምሮ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶችንና በንፁሃን ዜጎች ላይ ተፈፀሙ ጥቃቶችን በማቀናበርና በመደገፍ የፈፀማቸው ወንጀሎች እንዳሉ ሆኖ የሀገራችን መከታና የህዝባችን አለኝታ በሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን ላይ የክህደት ጥቃት በመፈፀም ሀገራዊ ክብራችንን ከመዳፈር ባለፈ ሉዐላዊነታችንንም ጭምር አደጋ ውስጥ የከተተ ከሃዲ ቡድን ነው፡፡ይህ ቡድን ፅንፍ በረገጠ የጥላቻ ስሜት እና በገነነ የገዥነት ደዌ የተለከፈ ከመሆኑ የተነሳ በመከላከያ ሠራዊታችን ዓባላትና በንፁሃን ዜጎች ላይ አስከፊ ጭፍጨፋ በመፈፀም ምን ያህል ጨካኝና አረመኔ መሆኑን በገሃድ አረጋግጧል፡፡እርግጥ ነው ባለፉት ጥቂት ቀናት የመከላከያ ሠራዊታችን የተቃጣበትን ጥቃት በመመከት የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና እነዚህን ከሃዲ ወንበዴዎች ለፍርድ ለማቅረብ ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል፡፡ ይህ ህግን የማስከበር እርምጃ ትክክልና ተገቢ ስለመሆኑ የሚጠራጠር ካለ እሱ አንድም ራሱ ከሃዲው ጁንታ አለበለዚያም የእሱ ተላላኪዎችና አሽቃባጮቹ ብቻ ናቸው የሚሆኑት፡፡ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን አሁን ላይ የጁንታውን የመጨረሻ ግብአተ-መሬት የማስፈፀም ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡በጣዕረ-ሞት ውስጥ የሚገኘው ይህ ወንጀለኛ ቡድን ቀደም ሲል በአምሳሉ የቀረፃቸውና የጥፋት ተልዕኮ ሰጥቶ ያሰማራቸው ቅጅዎቹ በክልላችን በተለይም በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች እየፈፀማቸው ያሉ እጅግ ዘግናኝና ሰብአዊነት የጎደላቸው የጥፋትና የሽብር ድርጊቶች መቼም ቢሆን ይቅር የማያስብሉ ናቸው፡፡ሰሞኑን በድባጢ ወረዳ ቂዶህ ቀበሌ በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀመው ከሰዋዊነትም ሆነ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ውጪ የሆነ ዕኩይ ተግባር የክፋቱን ጠርዝ እና የጭካኔውን ጥግ የሚያሳይ ፍፁም ሰይጣናዊ የሆነ እኩይ ተግባር ነው፡፡እንዲህ ዓይነቱ እኩይ ተግባር በዜጎች መካከል ዓመታትን የሚሻገር የቁርሾና አንዳንዴም ለትውልድ የሚተርፍ የበቀል ስሜት የሚያስቋጥር ከመሆኑ የተነሳ በህዝቦች አንድነትና በጋራ ሀገር ግንባታ ሂደት ላይ የሚደቅነው መሠናክል እና የሚከምረው እንቅፋት ሊሻገሩትም ሊንዱትም የሚከብድ መሆኑ አይቀሬ ነው፡፡በመሆኑም ወንጀለኞች እና ተባባሪዎቻቸው ከያሉበት ታድነው በፈፀሙት ወንጀል ልክ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የማድረጉ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ባፋጣኝ ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ፣ አስቸኳይ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ተገቢውን እርዳታ እንዲያገኙ እና የተፈጠረባቸው የመንፈስ ስብራት እንዲጠገን የማድረግ ሥራ በተለየ ትኩረት መሥራት ተገቢ ይሆናል፡፡ የአካባቢውን ሠላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥልት ቀይሶና ራሱን የቻለ የአሠራር ሥርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግም ያስፈልጋል፡፡በዚህ ረገድ የክልሉ መንግሥት ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስና ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እያከናወነ ያለውን ወንጀለኞችን አድኖ የመያዝ፣ የተፈናቀሉትን የማስመለስ፣ ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርሳቸው የማድረግ እና የአካባቢውን ሠላም በአስተማማኝ ሁኔታ የማረጋገጥ ሥራ ሁላችንም ልናግዝና አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ልናደርግ ይገባናል፡፡#የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

Leave a Reply