You are currently viewing በርካታ ቁጥር ያለው የህወሓት የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

በርካታ ቁጥር ያለው የህወሓት የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

  • Post comments:0 Comments

የህወሓት ቡድን ያሰማራቸው ልዩ ኃይሎችን በመደምሰስ በሺዎች የሚቆጠሩ ለውጊያ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡የታጣቂው ህወሓት ልዩ ኃይል በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣በአማራ ልዩ ኃይልና በሚሊሻ አባላት እየተደመሰሰ ይገኛል። በዚህ ታላቅ ጀብድ ሰራዊቱ የህወሓት ስግብግብ ኃይል ለጦርነት እየተጠቀመባቸው የነበሩ ከ230 በላይ ክላሽንኮቭ፣ ከ1 ሺህ በላይ የእጅ ቦምብና ሌሎች ተተኳሽ መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ዕዝ የሰው ሐብት ልማትና የሚዲያ አስተባባሪ ኮሎኔል ደጀኔ ጸጋዬ ተናግረዋል።እየተካሄደ ባለው ህግ የማስከበር ለህልውና ዘመቻ የአማራ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት በተሰጣቸው ቀጣና በጠላት ላይ ከባድ ወታደራዊ ጥቃት በመፈጸምና በመደምስስ ግዳጃቸውን በብቃት እየፈጸሙ መሆኑንም አመላክተዋል።የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት በትህነግ አፋኙ ቡድን ላይ እያከናወኑት ባለው ህግ የማስከበር ለህልውና ዘመቻ የአካባቢው ህዝብ የምግብና ሌሎች ድጋፎችን እያደረገ መሆኑንም አብመድ ዘግቧል።በሌላ በኩል የትምዕት አንዱ ቅርጫፍ የሆነው የሱር ኮንስትራክሽን ድርጅት ውስጥ በቃፍታ ሁመራ በርካታ የጦር መሳሪያ መያዙ ነው የተገለጸው።የሱር ኮንስትራክሽን ድርጅት ከባእከር ቃፍታ አዲረመጽ የመንገድ ስራ ተረክቦ የገነባው ካምፕ በአማራ ልዩ ኃይል ሲፈተሽ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተገኝተዋል።የአማራ ልዩ ኃይል የዘመቻ ኃላፊ ኮማንደር ምስጋናው ተሰማ እንደተናገሩት፣ የኮንስትራክሽን ድርጅቱ መንገድ እገነባለሁ በማለት የጦር መሳሪያ በማከማቸት የህወኃት የጦር አጋዥ በመሆን ሲሰራ እንደነበር በካምፑ ፍተሻ ስናደርግ ያገኘነው ጦር መሳሪያ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)

ምላሽ ይስጡ