You are currently viewing

  • Post comments:0 Comments

በአሁኑ ወቅት ከሀዲው የህወሃት ቡድን የኩራታችንና የሉዓላዊነት ምንጭ የሆነውን የመከላከያ ሰራዊታችን ማንም ባልጠበቀው ሁኔታ በመክበብ ጥፋት ለማድረስ ጥረት ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡ ይህ ስግብግብ ጁንታ ቡድን ህዝብን ለማበጣበጥ፣ወንድማማች ህዝቦችን ለመለያየትና አገራችንን ለማፈራረስ መቼም ቢሆን ወደኋላ እንደማይል ባለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት በግልጽ አሳይቷል፡፡

ስለሆነም ዜጎች በሁሉም የሀገራችን ክፍል የሰላም አየር እንዲተነፍሱና በነጻነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ ብሎም የጀመርነውን ሁለንተናዊ ለውጥ በማስቀጠል አመርቂ ለውጥ ለማምጣት እንዲቻል መንግስት እያካሄደ ያለውን ህግን የማስከበርና የህልውና ዘመቻ በውጤታማነት ለመፈጸም ከመንግስት ጎን በመቆም ዛሬም አጋርነታችንን ልናሳይ ይገባል፡፡

ምላሽ ይስጡ