በማይካድራ የተካሄደውን አሰቃቂ ግድያ የህወሓት ቡድን መፈጸሙን አምንስቲ አስታወቀ

በማይካድራ የተካሄደውን አሰቃቂ ግድያ የህወሓት ቡድን መፈጸሙን አምንስቲ አስታወቀ

  • Post comments:0 Comments

በትግራይ ክልል በማይካድራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የተካሄደውን አሰቃቂ ግድያ ከሃዲው የህወሓት ቡድን መፈጸሙን የሚያመለክት መረጃ ከአይን ዕማኞችና ከሳተላይት ምስል ማግኘቱን አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምንስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ።

አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ፖለቲካዊም ይሁን ወታደራዊ ተሳትፎ የሌላቸው የጉልበት ሰራተኞች እና ንጹሃንን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው እንደተገኙ መሰረቱን ለንደን ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ተቋም አስታውቋል።
አሰቃቂ የንጹሃን ግድያውን የህወሓት ሃይል መፈጸሙን ከአይን እማኞች በተገኘ መረጃ ማወቅ መቻሉንም የሰብአዊ መብት ተሟጋት ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

በማይካድራ በህወኃት የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ እየተወሰደ ባለው ህግን የማስከበር እርምጃ ላይ በምንም መንገድ የማይሳተፉና በቀን ሰራ የሚተዳደሩ ንጹሐን ዜጎች መሆናቸው በአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምንስቲ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተሩ ዲብሮሴ ሙቼና አስታውቀዋል፡፡ ይህም ድርጊት እጅግ አሰቃቂ አደጋ ነው ብለዋል፡፡

ከሀዲው የህወሓት ቡድን ልዩ ሀይል አባላት በመከላከያ ሰራዊትና በአማራ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻ እየተወሰደበት ባለው ህግ የማስከበር እርምጃ ሸሽቶ ሲወጣ ጥቅምት 30/2013 ዓ. ም ሌሊት በንጹሀን የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙ ይታወሳል ሲል ኢ.ፕ.ድ ዘግቧል።

Leave a Reply