የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

  • Post comments:0 Comments

አባገዳዎች ፣ አደ ስንቄዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተከበረው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር የፀጥታ ግብረ ኃይሉ ዕቅድ በማውጣት እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎቹን በማወያየት ወደ ስራ መግባቱን ኮሚሽኑ አስታውሶ ልዩ ልዩ አካላትን ያሳተፍ የፀጥታ ስራ በመሰራቱ በዓሉን በሰላም ማክበር እንደተቻለ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ለበዓሉ ስኬታማነት ትብብር ላደረጉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ የበዓሉ ተሳታፊዎች እና የፀጥታ አካላት በሙሉ ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።

Leave a Reply