የብልጽግና የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ስራ መሬት እንዲነካ ሁሉም የብልጽግና ጽ/ቤቶች እንደ አንድ የብልጽግና ቤተሰብ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ተጠቀሰ፡፡

የብልጽግና የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ስራ መሬት እንዲነካ ሁሉም የብልጽግና ጽ/ቤቶች እንደ አንድ የብልጽግና ቤተሰብ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ተጠቀሰ፡፡

  • Post comments:0 Comments

የብልጽግና ዋና ጽ/ቤት የዓለምአቀፍና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ከዘጠኙ ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ማድረግ ጀመሯል፡፡ በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ዋና ጽ/ቤት የዓለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ እንደጠቀሱት የፖለቲካ ስራው መሬት እንዲነካ ጠንካራ የህዝብ ግንኙነት ስራ መስራት ይገባል ያሉ ሲሆን ብልጽግና መሰረቱ አብሮነት በመሆኑ እንደ አንድ ቤተሰብ መንቀሳቀስ ይገባል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ብልጽግና የጠራና አገርን የሚያሻግር እሳቤ እንደያዘ ፓርቲ ይህ እሳቤ የሁሉም የህብረተሰባችን ክፍል እሳቤ እንዲሆን መሰራት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር ቢቂላ በውይይቱ መክፈቻ ላይ እንደጠቀሱት ይህ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተሰባሰበው የብልጽግና ኃይል ጠንካራ የብልጽግና ቤተሰብ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል፡፡በውይይቱ የእቅድና ሪፖርትን ጨምሮ የህዝብ ግንኙት ስራዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ መምራት የሚያስችል ስልጠናም የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በጽ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ክፍል የለማውና በአምስት የአገሪቱ ቋንቋዎች የተዘጋጀው ዌብሳይትና ክላውድ ስራ በይፋ የማስጀመር ስራ ይሰራል፡፡ከስልጠናው በኋላ ከሁሉት የአገራችን ክፍል የተሰባሰቡት የብለጽግና ቤተሰቦች እንደ አንድ ለብልጽግና ዓላማ የሚሰሩና የብልጽግና እሳቤዎችን የህዝባችን እሳቤ በማድረግ የአገራችንን ብልጽግና እውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

Leave a Reply