Skip to content
በፓርቲው መተዳደሪያ ደንቡ አንቀፅ 23(6) መሰረት ለኮሚሽኑ የተሰጡት ተግባራት እና ኃላፊነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤
- የፓርቲውን የፖለቲካ ጥራት እና የሥነ ምግባር ጤናማነት ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ክትትል ያደርጋል፤
- የፓርቲዉ ገንዘብ፣ ንብረትና ሰነዶች በአግባቡ መጠበቃቸውን ቁጥጥር ያደርጋል፣ የፓርቲው አባላት መዋጮ በወቅቱና በትክክል መሰብሰቡን ይቆጣጠራል፣ መዋጮ በወቅቱና በትክክል መሰብሰቡን ይቆጣጠራል፤
- የፓርቲው አባላትና አካላት መብቶች እና ጥቅሞች መከበራቸውን ይከታተላል፣
- ከአባላት የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ይቀበላል፣ ይመረምራል፣ የእርምት የውሳኔ ሐሳቡን ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና እንደ አግባቡ በየደረጃው ላሉ የፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ያቀርባል፤
- ዝርዝር የሥነ ምግባር፣ የኢንስፔክሽንና የቁጥጥር መመሪያ በማርቀቅ ለፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አቅርቦ ያጸድቃል፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፤
- የፓርቲ ሥነ ምግባርን ያሻሽላል፣ ሙስናን ለመዋጋት ጥረቶችን ያደርጋል፣ ያስተባብራል፤
- በየደረጃው የሥነ ምግባር ጥሰቶችን ይመረምራል፣ ተገቢውን የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- ከፓርቲው የፖለቲካ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በሚሰጥ ተልእኮ መሰረት አስፈላጊ ሆነው የተገኙ የምርመራ የክትትል እና የቁጥጥር ሥራዎችን ይሰራል፤
- በፓርቲው አካላት መካከል ልዩነት ሲኖር ወይም ፓርቲውን የሚመለከቱና መጣራት የሚገባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ፤ እንዲሁም በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ወይም ሥራ አስፈጻሚ በኩል ወይም በየደረጃው በሚገኙ የፓርቲው መዋቅር ጥያቄ ሲቀርብለት እንደ አንድ ነጻ አጣሪ አካል ሆኖ ያገለግላል፤ የራሱን የውሳኔ ሀሳብ ያካተተ ሪፖርትም ለማዕከላዊ ኮሚቴ ወይም ለሚመለከተው የፓርቲ መዋቅር ያቀርባል፤
- ኮሚሽኑ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንቡ የተሰጡትን ተግባራትና ኃላፊነቶች አስመልከቶ በየወቅቱ ኢንስፔክሽንና ልዩ ልዩ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ የጥናቱን ግኝቶች ከውሳኔ ምክረ ሐሳብ ጋር ለሚመለከታቸው የፓርቲ አካላት ያቀርባል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤
- ኮሚሽኑ ለሥራ የሚያስፈልገውን ዓመታዊ በጀት በማዘጋጀት እንዲፀድቅ ለማዕከላዊ ኮሚቴ ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ያስተዳድራል፣ ይመራል፤
- ለፓርቲው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ተገዢ ያልሆኑ የኮሚሽኑ አባላትን በ2/3ኛ ድምጽ ያግዳል፤
- ስለሥራው በማእከል ደረጃ ለፓርቲው ጉባዔ፣ እንዲሁም እንደአግባብነቱ በክልል እና አከባቢያዊ መዋቅሮች አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ ላለው ኮሚሽን ሪፖርት ያቀርባል፤
- ይህንን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በማድረግ የኮሚሽኑን የውስጥ የአሰራር መመሪያዎች ማውጣት ይችላል፡፡