You are currently viewing በዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የተመራ የኢትዮጵያ ልኡክ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያየ

በዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የተመራ የኢትዮጵያ ልኡክ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያየ

  • Post comments:0 Comments

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተመራ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ልኡክ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቮስግሉ ጋር ተወያየ።

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቮስግሉ ጋር በነበራቸው ቆይታም በወቅታዊ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል።

ውይይቱን አስመልክቶ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቮስግሉ በትዊተር ገፃቸው ፥ “የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ልዩ መልእክተኛ እና በቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ጋር ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል” ብለዋል።

ምላሽ ይስጡ