You are currently viewing በቢሾፍቱ ከተማ 2ተኛ ቀኑን የያዘው የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ዋና ጽ/ቤት የስልጠና መድረክ እንደቀጠለ ነው::

በቢሾፍቱ ከተማ 2ተኛ ቀኑን የያዘው የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ዋና ጽ/ቤት የስልጠና መድረክ እንደቀጠለ ነው::

  • Post comments:0 Comments
በቢሾፍቱ ከተማ እየተደረገ ባለው የዞን/ከተማ/ልዩ ወረዳ የኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች እያሳተፈ የሚገኘው የስልጠና መድረክ በሁለተኛው ቀን ውሎው 3 የመወያያ ሰነዶች ቀርበው ውይይት በመደረግ ላይ ይገኛል።
የውይይት ስነድ አቅራቢዎች ዶክተር ደስታ ተስፋው የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ የፓርቲ ዲሲፒሊን መመሪያ፣ አቶ መብራቱ ጉግሳ በኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት የሥነምግባር ዋና ዳይሬክተር የኮሚሽኑ የአቤቱታ አቀራረብና የአፈታት መመሪያ እንዲሁም አቶ አብርሃም ፋንቱ የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ቢሮ ሃላፊ የፓርቲ ሃብት አስተዳደር መመሪያዎችና የኮሚሽኑ ሚና የሚሉ ናቸው።
እነዚህ መመሪያዎች ኮሚሽኑ በብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ የተሰጠውን ሃላፊነት በብቃት መወጣት እንዲችል፣ በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ አመራሮች በቀጣይ የእለት ተእለት የኮሚሽኑን የስራ እንቅስቃሴ በእውቀት፣ በጥራትና በብቃት መፈጸም እንዲችሉ ብሎም ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ላቅ ያለ ፋይዳ ያላቸው በመሆኑ ስልጠናው እንዲሰጥ ተደርጓል።
ጠንካራ ኢንስፔክሽን፤ ለጠንካራ ፓርቲ!

ምላሽ ይስጡ