You are currently viewing የስልጠና መድረኩ ስለኮሚሽን የነበረውን ግንዛቤ ከፍ እንዲል አድርጓል ተባለ::

የስልጠና መድረኩ ስለኮሚሽን የነበረውን ግንዛቤ ከፍ እንዲል አድርጓል ተባለ::

  • Post comments:0 Comments
በኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት በተዘጋጀው የስልጠና መድረክ ላይ የተሳተፉ የፌዴራል ዞንና ወረዳ፣ የፓርላማ ልዩ ወረዳ እና የውጭ ጉዳይ ኮሚሽን አባላት በቀረበው ገለፃ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን በመመሪያዎች ላይ የተሰጠው ስልጠና በመተዳደሪያ ደንብ የተቀመጠውን ተግባርና ሃላፊነት በሚገባ መወጣት እንድንችል ግንዛቤ የፈጠረልን በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ፤ የኮሚሽኑን ተልዕኮ በሚገባ እንዲናውቅ ያስቻለን መሆኑን፤ የመመሪያዎች አተገባበርና ተደራሽነት: እንዲሁም በየደረጃው ከሚገኙ የፓርቲ አደረጃጀት ጋር በትብብር መስራት ጋር በተያያዘ በጥያቄና አስተያየት መልክ ከቀረቡ ጉዳዮች መካከል ተጠቃሾች ናቸው።
ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የአደረጃጀት ዘርፍ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አበበ: የኮሚሽኑ ጽ/ቤት የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር አቶ መብራቱ ጉግሣ እና የኮሚሽኑ ጽ/ቤት የሥነምግባር ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር አቶ ነስረዲን ማሐሙድ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የማጠቃለያ ሀሳብና አስተያየት የፓርቲው የኢንስፔክሽንና የሥነምግባር ኮሚሽን አባልና የኮሚሽኑ ጽ/ቤት ሃላፊ በሆኑት በአቶ ሀብታሙ ሲሳይ የተሰጠ ሲሆን በፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በኩል ለኮሚሽኑ ተገቢውን ትኩረት ተሰጥቶ ሁለንተናዊ ድጋፍ እየተደረገና በክልል/ከተማ የፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችም ተመሳሳይ ትኩረት እንዲሰጥ አቅጣጫ የተቀመጠ መሆኑን አንስተው: የስልጠናው ተሳታፊዎች የኮሚሽኑን ተልእኮ በሚገባ ተገንዝበው እና እነዚህን መመሪያዎች የስራ መመሪያ አድርገው በጊዜ የለኝም ቅኝት በሙሉ አቅም በመንቀሳቀስ እና ትይዩ ከሚገኙ የፓርቲ አደረጃጀቶች ጋር በቅንጅት በመስራት ኮሚሽኑ ለፓርቲው ጥንካሬ የበኩሉን ሚና መጫወት እንዲችል ሚናቸውን እንዲወጡ እንዲሁም በቀጣይ ለኮሚሽኑና ለፓርቲ አባላትና አመራር ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጠንካራ ኢንስፔክሽን፤ ለጠንካራ ፓርቲ!

ምላሽ ይስጡ