በስልጠናው በፌዴራል ተቋማት የሚገኙ አደረጃጀቶች ስለኮሚሽኑ የአሰራርና አደረጃጀት መመሪያ፣ የኮሚሽኑ የግምገማና የቁጥጥር መመሪያ፣ የኢንስፔክሽንና የቁጥጥር መመሪያ፣ የአቤቱታ አቀራረብና አፈታት መመሪያ እንዲሁም የፓርቲው አመራርና አባላት የዲስፕሊን መመሪያዎች ላይ ግንዛቤ እንዲጨብጡ በማድረግ ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት እውን ለማድረግ መድረኩ አጋዥ ስለመሆኑ የኮሚሽኑ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ገልጸዋል።
የኮሚሽኑ አባላት ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ በየአደረጃጀቶቻቸው ለሚገኙ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ መሆኑን የጽ/ቤት ሃላፊ አስታውቀዋል።
በአጠቃላይ ኮሚሽኑ በአምስተኛው የጋራ ምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል።
ጠንካራ ኢንስፔክሽን፤ ለጠንካራ ፓርቲ!