You are currently viewing የኮሚሽኑ 5ኛው የጋራ ምክክር መድረክ በስኬት ተጠናቋል።

የኮሚሽኑ 5ኛው የጋራ ምክክር መድረክ በስኬት ተጠናቋል።

  • Post comments:0 Comments
ላለፉት ሁለት ቀናት በጅግጅጋ ሲካሄድ የነበረው የ2016 በጀት አመት የ1ኛው መንፈቅ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ የኮሚሽኑ የስድስት ወራት ሪፖርት ላይ ተወያይቶ የጋራ ለማድረግ ተችሏል::
በተጨማሪም በተሻሻለ የኮሚሽኑ አደረጃጀትና አሰራር መመሪያ፣ የኮሚሽኑን የአቤቱታ አቀራረብና አፈታት መመሪያ እና የኮሚሽኑን የግምገማና የምዘና መመሪያ እንዲሁም በማዕከላዊ ኮሚቴ በጸደቀው የፓርቲ አባላትና የአመራር ዲሲፕሊን መመሪያ እና የኢንስፔክሽንና የቁጥጥር መመሪያዎች ላይ የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል።
በቀጣይ በሁሉም ክልሎችና የከተማ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መዋቅር አማካይነት ግንዛቤ የመፍጠርና መመሪያዎችን ተፈጻሚ የማድረግ ስራዎች እንዲተገበሩ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በመጨረሻም የሶማሊ ክልል ኮሚሽን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት መልካም አፈፃፀም ከቀረበ በኃላ የጋራ ምክክር መድረክ የጅግጅጋ ስምምነት(Jigjiga Resolution) በማውጣት ተጠናቋል::
ሰኞ፣ ጥር 27 ቀን 2016
ጅግጅጋ
“ጠንካራ ኢንስፔክሽን: ለጠንካራ ፓርቲ!”

ምላሽ ይስጡ