You are currently viewing የኮሚሽኑ አምስተኛው የጋራ የምክክር መድረክ መካሄድ ጀምሯል

የኮሚሽኑ አምስተኛው የጋራ የምክክር መድረክ መካሄድ ጀምሯል

  • Post comments:0 Comments
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የምክክር ኮሚሽኑ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ላይ የኮሚሽኑ ጽ/ቤት ሃላፊ ክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ የመግቢያ ንግግር አድርገዋል።
የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ ወደ ሶማሌ ክልል የብልጽግና ማሳያ ወደሆነችው የጅግጅጋ ከተማ እንኳን በደህና መጣችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፏል። በመልዕክታቸው ብልጽግና በለውጥ ጉዳና ላይ መሆኑን አመላካች ከሆኑት አንዱ በክልላችን የተፈጠረው ሰላምና በጅግጅጋ ከተማ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ግልጽ ማሳያ ናቸው ብለዋል። በቀጣይ ክልሉ ብሎም የጅግጅጋ ከተማ መሰል ስብሰባዎችንና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል። መላው ተሳታፊዎች ከዚህ ስትመለሱ ክልሉን በማስተዋወቅ የአምባሳደርነት ሚና እንድትወጡ አደራ በማለት መልካም የውይይትና ቆይታ ጊዜ ተመኝተዋል።
የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸው ኮሚሽኑ በእስካሁኑ እንቅስቃሴ አበረታችና ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን አንስተዋል። በዚህ የዕቅድ ግምገማ መድረክ ያለፈውን አፈጻጸም በሚገባ ገምግመን ጥንካሬያችንን ይበልጥ አጉልተን ድክመቶቻችንን አርመን ለመሄድ የሚያስችል የጋራ ምክክር የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰዋል። አክለውም ኮሚሽኑ በመተዳደሪያ ደንብ የተሰጡትን ሃላፊነቶች በብቃት ለመወጣት እንዲቻለን መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል። በመክፈቻ ንግግራቸው ጠንካራ ኮሚሽን እንዲኖረን ለማድረግ የፓርቲው ምክትል ፕረዚዳንት ናየብልጽግና ጽ/ቤት ሃላፊ የተከበሩ አቶ አደም ፋራህንና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊዎችን አመስግነዋል። በመጨረሻም ክብርት ሰብሳቢዋ የሶማሌ ክልል መንግስትና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮችና አባላት መድረኩ ስኬታማ እንዲሆን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በኮሚሽኑ ስም የከበረ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በውይይት መድረኩ የ2016 በጀት አመት አንደኛ መንፈቅ አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፓርት በክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ የኮሚሽን አባልና የፅ/ቤት ኃላፊ ቀርቦ ውይይት በመደረግ ላይ ይገኛል።
ጠንካራ ኢንስፔክሽን፤ ለጠንካራ ፓርቲ!

ምላሽ ይስጡ