You are currently viewing ከ580 ሚሊዮን ብር በላይ የተለያዮ የኢትዮጵያ ክልሎችና ባለሃብቶች ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስጦታ አበርክተዋል!!

ከ580 ሚሊዮን ብር በላይ የተለያዮ የኢትዮጵያ ክልሎችና ባለሃብቶች ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስጦታ አበርክተዋል!!

  • Post comments:0 Comments
ከ580 ሚሊዮን ብር በላይ የተለያዮ የኢትዮጵያ ክልሎችና ባለሃብቶች ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስጦታ አበርክተዋል!!
ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 580 ሚሊዮን ብር ስጦታ ተበረከተ።
በአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የምስረታ እና ይፋዊ የስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የታደሙ ወንድም
ህዝቦችና ባለሀብቶች ለክልሉ ማቋቋሚያ የሚሆን የገንዘብ ስጦታ አበርክተዋል።
በዚህም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 100 ሚሊዮን ብር ፣አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 60 ሚሊዮን፣
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት 30 ሚሊዮን ብር፣ ሶማሌ ክልላዊ መንግሥት 20 ሚሊዮን ብር ፣
አማራ ክልላዊ መንግስት 20 ሚሊዮን ብር፣ ሲዳማ ክልላዊ መንግስት 20 ሚሊዮን ፣ የደቡብ ምዕራብ
ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት 15 ሚሊዮን ብር ፣ አፋር ክልላዊ መንግስት 10 ሚሊዮን ብር፣ ቤንሻንጉል
ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት 10 ሚሊዮን፣ ጋምቤላ ክልላዊ መንግስት 5 ሚሊዮን ብር፣ ድሬዳዋ ከተማ
አስተዳደር 10 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ባለሀብት ፍሬው ቱፋ 50 ሚሊዮን ብር አበርክተዋል።
በተያያዘም በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች 215 ሚሊዮን 710 ሺህ 912 ብር፣ ከልማት ድርጅቶች 20 ሚሊዮን
300 ሺህ በአጠቃላይ ከክልሎች ፣ ዞኖችና ልማታዊ ባለሀብቶች 580 ሚሊዮን ብር በስጦታ ተበርክቷል።
በሥፍራው የተገኙ ክልሎች ተወካዮችም ሁላችንም ተጋግዘንና ተባብረን በመስራት የኢትዮጵያ
ብልጽግና እውን እናደርጋለን ብለዋል።

ምላሽ ይስጡ