የብሔር ብሔረሰቦች የአመታት ጥያቄ በፓርቲያችን መሪነት ምላሽ አግኝቷል – አቶ አደም ፋራህ
የብሔር ብሔረሰቦች የአመታት ጥያቄ በፓርቲያቸው መሪነት ምላሽ ማግኘት መቻሉን የብልጽግና
ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ይፋዊ ስራ ማስጀመሪያና ማብሠሪያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የዕለቱ
የክብር እንግዳ አቶ አደም ፈራህ፥ የህዝቦችን የዓመታት ጥያቄ ሠላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና በህዝቦች ነጻ ፈቃደኝነት
ላይ በተመሠረተ ህብረ-ብሔራዊ ክልል ፕሮግራም ላይ በመገኘታቸው የተሠማቸውን ደስታ በራሳቸውና በፓርቲው
ስም ገልፀዋል።
የህዝቦችን የከረመ ጥያቄ ሠላማዊ፣ ህዝብን ባሣተፈ፣ አንድነትን በጠበቀ መንገድ ምላሽ መስጠት የፓርቲያችን
መርህ ነው ሲሉ አጽንኦት ሠጥተዋል።
የሚነሱ ጥያቄዎች የወል እውነት የሚጸናበት፣ የሚያስተሳስሩና የጋራ አንድነትን የሚያጎሉ ሊሆኑ እንደሚገባ
አሳስበዋል።
ከዚህ አንጻር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያ ተምሳሌታዊ ክልል እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።