You are currently viewing የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ጠንካራ ሥርዓት እንገነባለን – አቶ አደም ፋራህ

የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ጠንካራ ሥርዓት እንገነባለን – አቶ አደም ፋራህ

  • Post comments:0 Comments
የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ዘላቂነት ያለው ጠንካራ ሥርዓት እንገነባለን ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ
ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡
አቶ አደም ፋራህ በአርባምንጭ ማዕከል ከ’ዕዳ ወደ ምንዳ’ በሚል መሪ ሐሳብ እየተሰጠ በሚገኘው
የአመራር ሥልጠና መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻልና ማሻሻያውም
ቀጣይነትና ዘላቂነት እንዲኖረው የሚያስችል ጠንካራ ሥርዓት እንገነባለን ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ÷ ያሉንን ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ብልጽግናን
ለማረጋገጥ በሚያስችል የተስተካከለ ዕይታ፣ የደረጀ እና የሐሳብ ፓርቲ ነው ብለዋል በንግግራቸው፡፡
ብልጽግናም ሆነ ሕዝቡ ከአመራሩ ብዙ እንደሚጠብቁ ያስገነዘቡት አቶ አደም÷ አመራሮች ከስልጠና
የሚያገኙትን ግብዓት ወስደው በየአካባቢያቸው ያሉ መልካም አፈፃፀሞች ተጠብቀው እንዲሰፉ
መትጋት ይገባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ልማቱን ለማፋጠን የሚስችል አቅም አመራሩ ከስልጠናው እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ምላሽ ይስጡ