You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሧቸው ዋና ዋና ነጥቦች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ3ኛው የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ያነሧቸው ዋና ዋና ነጥቦች

  • Post comments:0 Comments
• እስያን፣ አውሮፓን እና አፍሪካን የማገናኘት ፍላጎት ያለው የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም በጋራ
የማደግ መርሆዎች ላይ የተመሠረተ ትልቅ ዓለም አቀፍ የትብብር ተነሳሽነት ነው።
• የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እጅግ በተወሳሰበ እና ቀጣይነት ባለው ቀውስ ውስጥ እያለፈ ይገኛል፤
በተለይም የአየር ንብረት ለውጥ፣ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ ጎልተው የሚታዩ ችግሮች ናቸው።
• የጋራ ችግሮቻችንን ለመፍታት የተባበሩ እና የተቀናጁ እርምጃዎችን መውሰዳችን ችግሮችን
ተቋቁመን እንድንቀጥል ረድተውናል።
• ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እንደ ዓለም አቀፍ መሪዎች የሰብአዊነት፣ የፍትሕ፣ የመደመር፣
የፍትሐዊነት እና የርኅራሔ መርሆዎችን ልንደግፍ ይገባል።
• ኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ታሪካዊ የሥልጣኔ ባለቤት የሆነች፣ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ
ፈጣን ኢኮኖሚ እና ሰፊ የሰው ኃይል ያላት ሀገር ናት።
• ኢትዮጵያ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሰፊው እስያ መካከል አስተሳሳሪ
እና መግቢያ የሆነች ሀገር ናት።
• አፍሪካ በመጪው ጊዜ የዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ኃይል ባለቤት እንድትሆን የሚያስችላት
ወጣት የሰው ኃይል አላት።
• የአፍሪካ እና ቻይና ግንኙነት የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን በማሳደግ እና የንግድ ልውውጥን
በማሻሻል ረገድ ብዙ ርቀቶችን ተጉዟል።
• የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ በአፍሪካ በርካታ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ረገድ የጎላ ሚና አለው።
• የቤልት ኤንድ ሮድ ፎረም ትልቁ ተሻጋሪ የመሠረተ ልማት ፕሮግራም እንደመሆኑ የካፒታል ልማትን፣
ቴክኖሎጂን እና ልምድን በማምጣት ዘላቂ ዕድገት እንዲመዘገብ እያስቻለ ነው።

ምላሽ ይስጡ