You are currently viewing የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የሚሳተፉበት 2ኛ ዙር የስልጠና መድረክ በዛሬው እለት ተጀምሯል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የሚሳተፉበት 2ኛ ዙር የስልጠና መድረክ በዛሬው እለት ተጀምሯል፡፡

  • Post comments:0 Comments
የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የሚሳተፉበት 2ኛ ዙር የስልጠና
መድረክ በዛሬው እለት ተጀምሯል፡፡
ፓርቲያችን ብልፅግና በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ አመራሮቹን በክህሎት፤በልምድ እና
በእውቀት ለማብቃት ሰፊ ስራዎች በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ከምስረታው ጀምሮም በርካታ የሰልጠና መድረኮችን በማዘጋጀት የፖለቲካ አመራሩ እንደ ፓርቲ
የምንቀርፃቸው ስትራቴጂዎች፤ፖሊሲዎች እና ፕሮግራሞች በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ የማድረግ
አቅሙ እንዲዳብር ለማስቻል ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በዚህም የአመራሩን የአላማ እና የተግባር አንድነት ማሳደግ የሚችሉ፤ተልእኮን የመፈፀም አቅምን
የሚያካብቱ፤ የህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት እሳቤን የሚያበለፅጉ
ውጤቶች ሲመዘገቡ ተስተውለዋል፡፡
በዛሬው እለትም በ10 የስልጠና ማእከላት የተጀመሩ የስልጠና መርሀ ግብሮች ከዚህ በፊት
የተገኙ ውጤቶችን ለማሳደግ እና አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለሙ ናቸው፡፡
የሰልጠና ማዕከላቱ በአዲስ አበባ፤በአዳማ፤በሀዋሳ፤በአርባምንጭ፤በጅግጅጋ፤ በባህርዳር፤
በሚዛን አማን፤በደሴ፤ በጅማ እና በሆሳዕና የሚገኙ ሲሆን ከስልጠናው ጎን ለጎን ውይይቶች
እና የልምድ ልውውጥ የተሞክሮ መርሀ ግብሮች ተዘጋጅተዋል፡፡
በአዳማ ከተማ በተካሄደው የመጀመሪያው ዙር ስልጠና ላይ ከ2ሺህ በላይ አመራሮች ተሳታፊ
የነበሩ ሲሆን በዚህኛው ዙር ከ12 ሺህ በላይ አመራሮች የስልጠናው ተሳታፊ ናቸው፡፡

ምላሽ ይስጡ