ፓርቲያችን ብልፅግና የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ መላ ህዝቡን ባሳተፈ መንገድ ከፍተኛ
እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።
የሠላም አማራጭ ሠላምን፣ልማትንና አብሮነትን ያደረጃል።የሠላም መንገድ ለሁሉም ጉዳዮች
ድልድይና የተስፋ ብርሃን ሆኖ ያገለግላል።
የሠላም አማራጭ የሠላምን መሠረት ያፀናል፤ ለመልማት ጉልበት ይሆናል፤ አብሮ ለማደግ
አቅምና ብርታት ይሠጣል።
የግጭት መንገዶች የሚያስከትሉትን ኪሳራ፣ የጥላቻን ጉዳት ተገንዝቦ ለዘላቂ ሠላም መሥራት
እንደ ሀገር እና ህዝብ ጥቅሙ ዘርፈ ብዙ ነዉ።
ሠላም የስነ ልቦና ስንቅ ነዉ፣ አብሮ ለማደግ ድልድይ ነዉ። ስለሆነም ስለሠላም ሲባል ሁሉንም አማራጮችን
መተግበር ያሻል።በብልጽግና ፓርቲ የሚመራዉ መንግስት የሠላምን ታላቅ ፋይዳ ተገንዝቦ ፣ ዘላቂ ሠላምን
ለማስፈን እየሠራ ይገኛል።
ትልቁን ምስል ኢትዮጵያን የመገንባትን ጉዳይ ቀዳሚ ጉዳይ በማድረግ መንግስት የጀመረው የዘላቂ ሠላም
ግንባታ ሂደት እንዲፋጠን ሁሉም ተዋኒያን የየበኩላቸውን ማበርከት ይጠበቅባቸዋል፤ዘላቂ ሠላም የጋራ
የቤት ሥራ ነዉና።መልካም ሳምንት ይሁንላችሁ!!