You are currently viewing የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊዎች በዋና ፅ/ቤቱ ውስጥ የተገነባው ዲጅታል የመረጃ ዶክመንቴሽን ማእከልን ጎበኙ።

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊዎች በዋና ፅ/ቤቱ ውስጥ የተገነባው ዲጅታል የመረጃ ዶክመንቴሽን ማእከልን ጎበኙ።

  • Post comments:0 Comments
12 ሚሊዮን አባላት ያሉት ፓርቲን ሊመጥን የሚችል ዲጅታል የዶክመንቴሽን ማእከል ገንብተን አጠናቀናል።
አቶ ሳዳት ነሻ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ
የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊዎች በዋና ፅ/ቤቱ ውስጥ የተገነባው
ዲጅታል የመረጃ ዶክመንቴሽን ማእከልን ጎበኙ።
በቅርቡ ተመርቆ ለአገልግሎት ይበቃል ተብሎ የሚጠበቀው ከፍተኛ ወጪ ፈሰስ የተደረገበት የብልፅግና ፓርቲ
የመረጃ ክምችት ማእከል እጅግ ዘመናዊ በሆነ ሁኔታ የ21 ክፍለ ዘመን የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ባማከለ ሁኔታ የተገነባ ነው።
የመረጃ ማእከሉ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ ሲሆን መረጃን ለመሰነድ፣ለማሰራጨት እና ለማደራጀት አቅም
በሚሆን ሁኔታ ተገንብቶ ተጠናቋል።
ስለ ማእከሉ ገለፃ ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ካሊድ ሀልዋን እንደገለፁት ማእከሉ የተከማቹ
ዶክመንቶችን ለአጠቃቀም ቀላል አድርጎ ጥቅም ላይ ለማዋል ብሎም የሚስጥራዊ ሰነዶችን ደህንነት በጠበቀ መልኩ አመቺ በሆነ
ስርአት እየሰነዱ ለመሄድ ከፍተኛ ጥቅም መስጠት እንዲችል ለማድረግ ታስቦ የተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ከታችኛው አደረጃጀት እስከ ላይኛው ፅ/ቤት ድረስ የሚኖሩ መረጃዎች ተሰንደው በአግባቡ በማእከሉ ውስጥ የሚደራጁ ሲሆን
በፓርቲው ውስጥ የሚደረጉ ውይይቶች፣መድረኮች እንዲሁም ሲምፖዚየሞች በተገቢው መልኩ ተሰድረው የሚከማቹበት ማእከል ነው።
መረጃን በአግባቡ ከመሰነድ በተጨማሪም በፓርቲው ውስጥ የመረጃ ግልፅነት እና ፍሰት እንዲኖር ማእከሉ የሚያግዝ ሲሆን ኋላ ቀር
የሆነ የመረጃ አያያዝን በማስቀረት ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ለትውልድ የሚተላለፍ የመረጃ ቅርስ መሆን እንደሚችል ታምኖበታል።
በምስል፣በድምፅ እና በፅሁፍ ማእከሉ መረጃዎችን በ3 የተለያዩ መንገዶች የሚሰንድ ሲሆን ኋላ ቀር አሰራርን የማስቀረት ፋይዳው
የላቀ መሆኑን የፓርቲያችን የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሳዳት ነሻ ገልፀዋል።
12 ሚሊዮን አባላት ያሉት ፓርቲን የሚመጥን የመረጃ ማእከል እንደሆነ እና በቅርቡም ለውስጣዊ
አስተዳደር ስራዎች አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተናግረዋል።

ምላሽ ይስጡ