You are currently viewing ብልጽግና የሚከተለው አቅጣጫ…

ብልጽግና የሚከተለው አቅጣጫ…

  • Post comments:0 Comments
ብልጽግና የሚከተለው የዴሞክራሲ አቅጣጫ
በትብብርና ውድድር ላይ የተመሰረተ፤ለብዝሃነትና ለህብረ ብሔራዊነት የተለዬ ቦታ የሚሰጥ፣የመግባባት ዴሞክራሲ ነው፡፡በህገ መንግስታችን ላይ የተመለከተውን እውነተኛ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትና ህብረ- ብሔራዊ ፌዴራሊዝም የመገንባት ዓላማ አለው፡፡
ብልጽግና የሚከተለው የኢኮኖሚ አቅጣጫ
በኢኮኖሚ ረገድ ብልጽግና የሚከተለው እሳቤ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረገ፣የመንግስትን ጣልቃ ገብነት የሚፈቅድ፣አካታች ካፒታሊዝም ነው፡፡የሚነደፉት የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ፕሮግራሞችና ስትራቴጂዎች በዋናነት ደሃ ተኮር ናቸው፡፡
ብልጽግና የሚከተለው የውጭ ግንኙነት አቅጣጫ
በውጭ ግንኙነት ረገድ ብልጽግና የሚከተለው እሳቤ በትብብርና በፉክክር መካከል ሚዛን የሚጠብቅ፣ለዜጎች ክብር ቅድሚያ የሚሰጥ፣ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ እና ለጎረቤት አገራት ቅድሚያ የሚሰጥ አቅጣጫ ነው፡፡በዚህ መንገድ የሚቃኙ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ተግበራዊ ያደርጋል፡፡

ምላሽ ይስጡ