ብልጽግና ፓርቲ የህዝብን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ፣ሙስናን የመታገልና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
በፖለቲካው መስክም ቢሆን ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ወደ ኋላ ያስቀሩ የፖለቲካ ባህልን በማስቀረት ታፋሪና ተከባሪ የሚያደርግ አዲስ አገራዊ አስተሳስብ እውን የማድረግ ጥረቶች ቀጥለዋል፡፡
ብዝሃነትን፣ሕብረ ብሔራዊነትና ሚዛናዊነትን የተቀበለ፣በፍትሃዊነትና እኩልነት መርህ የሚመራ፣ለዜጎች መብት ቅድሚያ የሚሰጥና የአገር በቀል እሴቶችን ያካተተ ስርዓት መገንባት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል።
ውስጠ ዴሞክራሲ ማጎልበት፣በትምህርትና ስልጠና በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የሰለጠነ የሰው ሃይል መገንባት፣በማህበራዊ ልማት የጀመራቸውን አመርቂ ውጤቶች ማስፋት የብልጽግና ፓርቲ ተልዕኮ ነው።
በየወቅቱ በሚያጋጥሙ ፈተናዎች ሳይበገር ህዝቡ ከፓርቲው ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ለመውሰድ በሚደረገው ጥረት ድጋፉን ማጠናከር እና ሁለንተናዊ ብልጽግናዋ የተረጋገጠች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት መደገፍ ይገባል።