ሸኔን በሚመለከት በሽብር መንገድ ዘላቂ ሰላም ማምጣት አይቻልም፤የወለጋ ሸኔና የሸዋ ሸኔ በሚል እርስ በእርሳቸው እየተዋጉ ይገኛሉ፤
የጦር መሳሪያ ታጥቆ ሰላምን ማረጋገጥ አይቻልም፤ምንጊዜም ሰላምን ማረጋገጥ የሚቻለው በውይይት እና በንግግር ብቻ ነው፤
በሽብር የሚገኝ ነጻነት፣ ሰላም እና ዴሞክራሲ የለም። የሸዋና የወለጋ ሸኔ እያለ እርስ በርሱ ሲዋጋ የሚውል ማእከላዊ እዝ የሌለው ሀይል ነው። ለኦሮሞ ሕዝብ እቆማለሁ ብሎ ኦሮሞን ይገላል ኦሮሚያን ያፈርሳል።
እኛ ግን አቋማችን አንድ ነው። በሀይል የሚገኝ ጥቅም የለም፣ ህገ መንግስት፣ ክልል ስርዓት ላይ መነጋገር እንችላለን፣ ነገር ግን በሃይል የሚገኝ ጥቅም የለም ብለን እናምናለን።