You are currently viewing ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት…

ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት…

  • Post comments:0 Comments

ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት እርስ በእርስ በመከባበር፣ በመቻልና በመቻቻል፣ የእርስ በእርስ ትብብርን እና ድርድርን ዋጋ በሚያረጋግጥ የዜጎች መስተጋብር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ለህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት መሰረቱ መከባበር፣ መደማመጥ እና መቻቻል ነው።

ብልጽግና ፓርቲ አሁንም የውስጠ ፖለቲካችንን ተገዳዳሪ አቅም ከመከባበራችን እና ከመደማመጣችን አቅጣጫ መፈተሽ ይኖርብናል ብሎ ያምናል፡፡ በብልፅግና እሳቤዎች ህዝባችንን ስንመራ በእርግጥም ህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነትን ያስቀደመ አመራር ነው እያረጋገጥን ያለነው? ብለን ውስጠ ፖለቲካችንን መፈተሽ ይኖርብናል፡፡

የግል ተጠቃሚነትና ስልጣንን ሽፋን ያደረገ የመልካም አስተዳደር ችግር ባልተቀረፈበት የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ምን አይነት ወንድማማችነት ነው የሚረጋገጠው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ለራስ ጥቅም ሲባል የሚሰዋ የብልፅግና እሴት መኖር የለበትም፡፡

ወንድማማችነት እንኳንስ በህብረ-ብሄራዊ ደረጃ ይቅርና በቤተሰብና በስጋ ዝምድና ደረጃም ብርቱ ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ እርስ በእርስ መተዛዘንና መተሳሰብ፣ ለህዝባዊ እና አገራዊ ተልዕኮ ራስን የበለጠ ዝግጁ ማድረግ ለህብረ-ብሄራዊ ወንድማማችነት መሰረት ነው፡፡

ምላሽ ይስጡ