You are currently viewing የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራም…

የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራም…

  • Post comments:0 Comments

የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራም ሦስት ግቦችን አካቶ ይዟል፡፡

  1. ጠንካራና ቅቡል ሀገረ-መንግስት በጽኑ መሰረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል ሀገራዊ መግባባት መፍጠር
  2. በተቋማዊና ህዝባዊ ባህል ላይ የቆመ የዴሞክራሲ ስርዓት መገንባት
  3. ዘላቂና አዎንታዊ ሰላምን ማረጋገጥ ናቸው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራም

  • የፓርቲያችን የፖለቲካ ፕሮግራም ዋነኛ ዓላማ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው፣ የብሔር ማንነትን እና የሀገራዊ አንድነትን ሚዛን የጠበቀ ሀገረ-መንግስት መገንባት ነው፡፡
  • ከጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ አንፃር ፓርቲያችን ህዝብ ከቀጥተኛ የህልውና አደጋ ተጠብቆ የልማት፣ የእኩልነት እና የነፃነት ፍላጎቶቹ እንዲሟላለት የሚያስችል ነፃ፣ ገለልተኛና ብቃትን መሰረት ያደረገ ሀገራዊ ተቋማዊ አደረጃጀት መገንባት ያስፈልጋል ብሎ ያምናል፡፡
  • በመሆኑም የሀገረ-መንግስት ግንባታ ጅምራችን ጠንካራና የማይናወጥ ተቋማዊ መሰረት ያለው እንዲሆን የብልጽግና ፓርቲ ግቡ አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡፡ የብልጽግና ፓርቲ ዴሞክራሲን በተቋማዊና ህዝባዊ ባህል ላይ መገንባት አስፈላጊ እንደሆነ ይገነዘባል፡፡
  • በሌላ በኩል ከሀገረ-መንግስት ቅቡልነት አንፃር የብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግስት ጥንካሬን ለማሳደግ በህገ-መንግስት የተቀመጠውን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመፍጠር ግብ ለማሳካት ይሰራል፡፡
  • በመሆኑም የሀገረ-መንግስቱን ቅቡልነት በሚጨምሩና ሀገራዊ መግባባትን በሚያመጡ፣ የህዝቦችን ግንኙነት በሚያሳልጡ እና የእውነተኛ እርቅ መንፈስን በሚያጎለብቱ ፖለቲካዊ እርምጃዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡፡
  • ፓርቲያችን የሀገረ-መንግስት ግንባታችን ህብረ-ብሔራዊ ማንነትን የተላበሰና ብዝሃነትን የሚያንፀባርቅ መሆን እንዳለበት በጽኑ ያምናል፡፡

ምላሽ ይስጡ