ብልጽግና ፓርቲ አዳጊና ተራማጅ ለሆነ አዳዲስ አስተሳሰብ የተዘጋጀ ተለማጭ የፖለቲካ ፍልስፍና የሚከተል ፓርቲ ነው፡፡
- ተራማጅ የዴሞክራሲ ስርዓት በሚፈልግ መሰረታዊ የፖለቲካ ኢኮኖሚ አመክንዮ መፈታት ያለባቸው ውስጣዊ ችግሮች እልፍ በሆነበት አገርና ማህበራዊ መስተጋብር ውስጥ የብልፅግና ተራማጅ እሴቶች በእርግጥም ወቅታዊና አስፈላጊ ናቸው፡፡
- ብልጽግና ገና ከመነሻው የአገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ እንደሚባለው ለአገር በቀል ችግሮች አገር በቀል መፍትሄ ያስፈልጋቸዋል ብሎ የተነሳ ፓርቲ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ለአገር በቀል አስተሳሰብና የመፍትሄ አማራጮች ተገቢውን ትርጉም መስጠት ችሏል፡፡
- ሁሉም ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ከውጪ በሚቀዱ የፖለቲካ አስተሳሰቦች አይፈቱም የተባለ ይመስል የግድ ከአገር በቀል የመፍትሄ አማራጮች ውጭ ሙሉ ለሙሉ ከውጭ በተቀዱ ርዕዮተ አለማዊ ፍልስፍናዎች መጠመድ የለብንም ብሎ የሚያስብ ፓርቲ ነው፡፡
- ስለሆነም የውስጥ ችግራችንን ለመቅረፍ የምንዋሰው ሌላ ባዕድ አስተሳሰብ ሳያስፈልገን እንደነገሩ ድንበር ተሻጋሪ መልካም ተሞክሮዎችን እየቀላቀልን ከችግሮች መላቀቅ እንችላለን፡፡ በዚህም አገር በቀል ብልሀት ችግሮቻችንን መፍታት ጀምረናል፡፡