You are currently viewing የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብዙ ተስፋዎች…

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብዙ ተስፋዎች…

  • Post comments:0 Comments
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብዙ ተስፋዎች የተጣሉበት ግን ደግሞ በበርካታ ፈተናዎች የተከበበ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡መንግስት አገራዊ ኢኮኖሚው ከገባበት ቀውስ ለማውጣት በ2011 ዓ/ም ይፋ ያደረገው እና በ2012 ዓ/ም ወደ ትግበራ የገባው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመሰረታዊነት ለመፍታት እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡
የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ተከትሎ መንግስት ተጨባጭ እርምጃዎችን በመውሰድ ግብርናን በማዘመን ረገድ የሰራቸው ስራዎች ተስፋ ሰጪዎች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ለግብርና አስፈላጊ የሆኑ በርካታ የግብርና ግብዓቶች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በማድረግ ግብርናውን የማዘመን ስራው መሰረት እንዲኖረው የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
ኢኮኖሚውን በበለጠ ሁኔታ ውጤታማ ሆኖ የተፈለገውን ግብ ለማምጣት እንዲቻል ለግብርና ስራው የምንሰጠውን ትኩረት ማጠናከርና ተገቢውንን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡አርሶና አርብቶ አደሩን በቅርብ ሆኖ ተገቢውን እገዛ በማድረግ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በጦርነት የተጎዳው ኢኮኖሚያችንን ማሳደግ ይኖርብናል፡፡

ምላሽ ይስጡ