You are currently viewing ለጋራ ብልጽግናችን በጋራ ቃል ኪዳን የምንገባበት ጉባኤ  /በሚራክል እውነቱ/

ለጋራ ብልጽግናችን በጋራ ቃል ኪዳን የምንገባበት ጉባኤ /በሚራክል እውነቱ/

  • Post comments:0 Comments

35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የፊታችን ጥር 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፤ የአፍሪካ መዲና፣ የዓለም ሦስተኛዋ የዲፕሎማሲ ማዕከልና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባችን ቀደም ያለ ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን እየተቀበለች ትገኛለች።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነት ተምሳሌት፣ ለአፍሪካ ነጻነት ግንባር ቀደም ሚና የተጫወተች፣ አፍሪካውያን አንድ ሆነው ጠንካራ ህብረት እንዲመሠርቱ የማዕዘን ድንጋዩን ያስቀመጠች ሀገር ነች።አፍሪካውያን እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ወደ ሌላ ሀገር እንደሚመጡ አይሰማቸውም፡፡ የሚመጡት ወደ ሀገራቸው ነውና፣ የሚሰበሰቡት በሀገራቸው ነውና፣ የሚመላለሱትም በሕዝባቸው መካከል ነውና።

ለ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና ለ40ኛው ለህብረቱ የሥራ አስፈፃሚዎች ጉባኤ ለመሳተፍ የአገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ መሆናቸው ይታወቃል።ስለሆነም ይህን ታላቅ ጉባኤ ከጉባኤ ባሻገር አፍሪካዊያን ያላቸውን ወንድማዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያስተሳስር በመሆኑ እንዲሁም የአገራችንን ወቅታዊ ትክክለኛ ሁኔታ ለአፍሪካዊያን የምናሳይበት ዕድል በመሆኑ በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባናል፡፡

በዚህ ወቅት 35ኛው የአፍሪካ መሪዎች መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ መደረጉ የሚያመጣው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ከፍታ እንደተጠበቀ ሆኖ እየሰራነው ላለው የዲፖሎማሲ ስራ ውጤታማነት የሚያበረክተው አስተዋጾኦ በእጅጉ ከፍ ያለ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን በአጠቃላይ የአለም ጥቁር ህዝቦች የአሸናፊነት ቀንዲል ናት፡፡ በአልበገርም ባይነት የምትታወቅ የአፍሪካውያን የነጻነት ተምሳሌትም ናት፡፡ኢትዮጰያውያን ከቀድሞ ጀምሮ ሉዓላዊነቷን የማታስደፍርና ለጥቁር ህዝቦች ነጻነትም ስትሟገት የቆየች አገር ናት ስትሆን ዘንድሮም በተለያየ መልኩ የገጠሟትን የውጭ ተጽዕኖና የውስጥ አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን በጽናት ስትታገል ቆይታለች። ይህንን የተረዱት አፍሪካዊያን ወንድሞቻችን እምቢ ለባርነት በማለት የድጋፍ ድምጻቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል፡፡

በመጪው ጥር 28 እና 29/2014 ዓ/ም በመዲናችን አዲስ አበባ የሚካሄደው 35ኛው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ይህንኑ አህጉራዊ አንድነታችንን አጠናክረን ለጋራ ብልጽግናችን በጋራ ለመነሳት ዳግም ቃልኪዳን የምንገባበት ትልቅ ጉባኤ ነው፡፡

ምላሽ ይስጡ