You are currently viewing የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አመራርና ሰራተኞች 16ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አከበሩ

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አመራርና ሰራተኞች 16ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አከበሩ

  • Post comments:0 Comments
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት አመራርና ሰራተኞች 16ኛውን የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አከበሩ
በብልጽግና ዋና ጽ/ቤት የአስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዓሉን ስናከብር በጁንታው ላይ እየተቀዳጀን የምንገኘውን ድል የአገሪቱን ህብረብሄራዊ አንድነት በማረጋገጥና በሌሎችም መስኮችን እንደግማለን ብለዋል፡፡
ለብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል *እንኳን አደረሳችሁ* በሚል መልዕክታቸውን የጀመሩት አምባሳደሩ የዘንድሮ በዓል ከበፊት የተለየ የሚያደርገው የፓርቲያችን ፕሬዘዳንት ለአገራችን ሉዓላዊነት በጦር ሜዳ እየተዋደቁ ከመላው የጸጥታ ሃይሉ ጋር በመሆን ድልም በማስመዝገብ ላይ ባሉበት ወቅት መሆኑ ነው ፡፡
ጠ/ሚኒስትራችና መላው የጸጥታ ሃይል ለአገራችን እየከፈሉት ያለውን መስዋትነት የጽ/ቤታችን አመራሮችና ሰራተኞችን ከጎናቸው በመሆን የበኩላችን እየተወጡ መሆናቸውንና ለወደፊቱም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ አገሪቱ ርዕስ ብሔርና ከፍተኛ የመንግስትና የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ‘ወንድማማችነት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት’ በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ምላሽ ይስጡ