የማያቋርጥ ህዝባዊ ደጀንነት ለሰራዊታችን ሁለንተናዊ ድል መሰረት ነው፤
**********************************************************************
በጋሸና ግንባር ንጹሃን ላይ ጥቃት የሚፈጽመው ወራሪ ቡድን በመከላከያ ሰራዊት፣በልዩ ሃይሎቻችንና በህዝባዊ ሚሊሻዎች በተቀናጀ የማጥቃት ስልት ተገቢውን ቅጣት በማግኘቱ ስትራቴጂክ ቦታ ያለውን የጋሸና ግንባር ከባድ መሳሪያዎችንና ተተኳሾችን ጥሎ እግሬ አውጪኝ ብሎ እየፈረጠጠ ይገኛል።
ሰራዊታችን በሚገኝባቸው የአውደ ውጊያ ግንባሮች ሁሉ አስፈላጊውን የደጀን ሕዝብ ድጋፍ እያገኘ ጠላት በሃይል የወረራቸውን አካባቢዎች እያስለቀቀ፤ በሕዝብ አለኝታነት ታግዞ ከፍተኛ ድል በወራሪው ቡድን ላይ እያስመዘገበ ስለመሆኑ በርካታ ማሳያዎችን ማንሳት ይቻላል።ሰራዊታችን ከአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ጋር ባሳየው ድንቅ ቅንጅት የላሊበላን ከተማ ከጠላት ጦር ነጻ ማውጣት ተችሏል።
ጠላት የኢትዮጵያን ሕዝብ በማጎሳቆል አገር የማፍረስ ዓላማውን ለመፈጸም ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ቢንቀሳቀስም በሰራዊታችን፣በልዩ ሃይሎቻችንና በሚሊሻዎቻችን ክንደ ብርቱነት የሚገባውን ቅጣት እንዲያገኝ ተደርጓል።
ጠላት በአፋርና በአማራ ክልሎች ላይ ወረራ በፈጸመባቸው እና ሕዝብ በተሰበሰበባቸው አካባቢዎች ላይ ከባድ መሳሪያ በመጣል፣ወጣቶችን በጅምላ በመረሸን፣ሴቶችን በመድፈርና ንጹሃንን በማሸበር የጭካኔ ጥጉን በድፍረት አሳይቷል።
ጠላት የያዛቸውን አገልግሎት መስጫዎች በተለይም ትምህርት ቤቶች፣ ሕክምና ጣቢያዎች እና የተለያዩ ተቋማትን የጥቃት ኢላማ በማድረግ የበለጠ ውድመት እንዳያደርስ ህዝቡ ራሱን አደራጅቶ ንብረቱን ከጠላት መጠበቅ ይገባዋል።
መከላከያ ሰራዊታችንም ይህን አሸባሪ አውዳሚ ቡድን እግር በእግር በመከታተል አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰደበት ይገኛል። አሸባሪው ቡድን ኢትዮጵያን የማተራመስ ፍላጎቱን እንደያዘ ዳግም በማያንሰራራበት መልኩ እየተመታ ይገኛል።
የሽብር ቡድኑ ግፍ የተመለከተው ሕዝብም ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ ቡድኑን ሌት ተቀን መግቢያ መውጫ እያሳጣው ይገኛል።ይህ ህዝባዊ ደጀንነት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል።