የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ዛሬ በተለያዩ መድረኮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተናገሯቸውን ንግግሮች እና መግለጫዎች ያካተቱ ሦስት ‹ከመጋቢት እስከ መጋቢት› ጥራዞች ይፋ አደረገ።
ንግግሮቹ እና መግለጫዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፉት ሶስት አመታት በሀገራዊ ፣ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን እሳቤ አቋም የሚያንፀባርቁ ናቸው።
የፊታችን መስከረም 24 ቀን 2014 በኢትዮጵያ ከሚደረገው አዲስ የመንግሥት ምስረታ ቀደም ብሎ የቀረበው ይህ ስብስብ በመጋቢት 2010 የመንግስት ሽግግር ከተደረገ በኋላ በተደረጉ ንግግሮች እና መግለጫዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተተገበሩ የተለያዩ ቁልፍ የመንግስት ሥራዎችን በታሪክ ለማስመዝገብ ያለመ ነው።