You are currently viewing ኢትዮጵያ ወኪሎቿን መርጣለች!

ኢትዮጵያ ወኪሎቿን መርጣለች!

  • Post comments:0 Comments
ኢትዮጵያ ወኪሎቿን መርጣለች!
ህዝብ በማን ሊወከል እንደሚገባው፣የማን ራእይ ለሀገር እንደሚጠቅም በሚገባ መርምሮ ድምፁን ሰጥቷል።
የምርጫ ሂደቱም በአለምአቀፍ ደረጃ በጎ እውቅና የተቸረው፣የዴሞክራሲ ልምምዳችንን አንድ እርምጃ ያሻገረ፣በኢትዮጵያውያን ዘንድ ቅቡልነት የታየበት፣ሰላማዊ ሂደትን የተላበሰ ነበር።
ይህንን የምርጫ ሂደት እና የህዝብ ከልብ የመነጨ የውክልና ድምፅ ከውስጥ ፍላጎታቸው የተነሳ እውቅና ያልሰጡት ዳግም የበረሀው ሽፍታ ቡድንን ለማንገስ የሚውተረተሩ በኢትዮጵያ ውስጥ በህዝብ ውክልና የተመረጠ ህጋዊ መንግስት እንዳይፈጠር የሚፈልጉ ናቸው።
ይህም ሴራ ለበስ አካሄድ እና ኢፍትሀዊ የሆነ ጫና በሀገራችን ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲጠናከር እያደረገ ይገኛል።
ነገር ግን ወኪሎቿን በካርዷ ያስመረጠችው ኢትዮጵያ ይህንን ጊዜ በህዝቧ ድጋፍ እና በአመራሮቿ ብልሀት እንደምትሻገረው ምንም ጥርጥር ሊኖር አይገባም።
ኢትዮጵያ ሁሌም ቢሆን አሸናፊ ናት።

ምላሽ ይስጡ