You are currently viewing የኢትዮጵያ እና የቱርክ አራቱ ስምምነቶች

የኢትዮጵያ እና የቱርክ አራቱ ስምምነቶች

  • Post comments:0 Comments
የኢትዮጵያ እና የቱርክ አራቱ ስምምነቶች
ኢትዮጵያ እና ቱርክ በትናንትናው እለት አራት ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
የኢትዮጵያ እና የቱርክ የሁለትዮሽ ግንኙነት 125ኛ ዓመት ላይ የተከናወነ ሲሆን፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ያደረጉት ይፋዊ ጉብኝት አራት ስምምነቶችን በመፈራረም ተጠናቋል።
በዚህም በውሀ ዘርፍ ትብብር ለማድረግ የጋራ መግባቢያ ሰነድ፣ የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት፣ የፋይናንስ ድጋፍን የተመለከተ የትግበራ ሰነድ እና የወታደራዊ ፋይናንስ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
በጉብኝቱ መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአኒትካቢር መካነመቃብር የመታሰቢያ ጉንጉን አስቀምጠዋል።
“ኢትዮጵያ ከቱርክ ጋር ያላት ትስስር በመከባበር እና በመተማመን የጋራ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ የበለፀገ ባህል እና ትውፊት ለሞላቸው ሁለት የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤቶች የሚመጥን ነው” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን በቤተመንግሥት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ደማቅ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ፥ ሁለቱ መሪዎች ከልዑካን ቡድኖቻቸው ጋር በመሆን የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱም ሁለቱም ወገኖች ትብብሩን በቀጣይነት ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለጻቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምላሽ ይስጡ