You are currently viewing በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለመምከር ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ ሴቶች ጋር ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል

በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለመምከር ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ ሴቶች ጋር ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል

  • Post comments:0 Comments
በወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለመምከር ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ ሴቶች ጋር ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል
 
የአቋም መግለጫው ከዚህ በታች እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
 
ኢትዮጵያ አገራችን የራሷን ጉዳይ በራሷ የመፍታት አቅም እና ችሎታም ያላት እና በታሪኳ ማሸነፍን እንጂ መሸነፍን አስተናግዳ የማታውቅ እና እኛም ህዝቦቿ የአድዋ ትውልዶች መሆናችንን እሳወቅን ማናቸውም ኃላያላን ነን ባዮች በአገራችን የተለያዩ ጫናዎችንና ጣልቃገብነትን እያሳዩ አገራችንን የሚፈታተኑ ሐይሎች መታገስ የማንችል መሆናችንን ከታሪካችን እንዲረዱ እና እጃቸውን ከኛ ኢቲዮጲያዊያን ሴቶች እንዲያነሱልን በአንድነት ድምጻችንን እያሰማን አገራችን ወደ ቀድሞ ሰላሟን እንድትመለስና ያላትን የመከባባር፣ የመተሳሰብና የመረዳዳት ባህሏን በማጎልበት ከምንጊዜውም በላይ አንድነታችንን አጠንክረን መስራት ይኖርብናል ፡፡
 
በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት እንደሀገር የገጠመንን የውስጥና የውጭ ፈተና በመመከት አገራችን ሰላሟን በማረጋገጥ የሀገር ሉአላዊነታችን ለማስጠበቅ እኛ ኢትዮጲያዊያን ሴቶች ከዚህ በታች የምንገልጻቸውን ባለ ስድስት አምስት ነጥቦች የአቋም መግለጫ አዘጋጅተናል፡፡
 
1. እኛ የኢትዮጵያ ሴቶች በሀገራችን ሉኣላዊነት ላይ እየተቃጣ ያለውን የውጭ ጣልቃ ገብነት እና የውስጥ ጠላቶቻችን ለመመከት አንድ ሁነን በተደራጀ መንገድ የጎላ ድምፃችንን እናስተጋባለን፡፡ አንድም ሁነን ጠንካራ ክንድ እንሰነዝራለን፡፡
 
2. እኛ የኢትዮፐጲያ ሴቶች መከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመቆም ሀገር የማደንን እና ሉዓላዊነትን የማስከበር ዘመቻ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ማለትም የስንቅ ዝግጅት፣ የደም ልገሳ፣ የዘማች ቤተሰብ በመደገፍ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን የመደገፍ እና የመንከባከብ እንዲሁም እስከ ግንባር በመሄድ ሰራዊቱን በመቀላቀል ለሰራዊቱ አስተማማኝ ደጀን እንሆናለን
 
3. እኛ የኢትዮጲያዊያ ሴቶች ለትግራይ ክልል እናቶች እና ሴቶች ያለንን ክብር እና ፍቅር እየገለጽን፤ ከዚሂ እኩይተግባር ፈጻሚ ቡድን ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በመነጠል የእህትማማችነት እሴቶቻችንን በማጎልበት ለአሸባሪ ቡድን ህይወታቸውን እየገበሩ ያሉትን ልጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በመታደግ ከጎናችን እንዲቆሙ በመላው የኢትዮፒያ ሴቶች ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!
 
4. እኛ የእትዮጵያ ሴቶች በተሰማራንባቸው የስራ መስኮች ሁሉ በንቃት እና በቁርጠኝነት በመንቀሳቀስ የአገራችንን የኢኮኖሚ እድገት ከሚያቀጪጩ እና ለተረጅነት ከሚጋብዙ አዝማሚያዎች እንታደጋታለን፡፡
 
5. በአሸባሪው የህውሃት ቡድን በሴቶች እና በህጻናት ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት እና እንግልት እንዲሁም የዜጎች መፈናቀል እናወግዛለን ይህነንም የአለም መንግስታት እንዲረዱልንና እንዲያወግዙ እንጠይቃለን፡፡
 
6. አገራችን እትዮጵያ የአድዋ ታሪክ ባለቤት ፣ ጀግንነት፣ የአሸናፊነት ታሪኳ እንዲቀጥል እና ዘላቂ ሰላሟ እንዲሰፍን በሁሉም ዘርፍ የበኩላቺንን ሚና እንጫወታለን፡፡
 
ኢትዮጵያ ሰላሟን ይመለሳል በልጆቿ ታፍራ እና ተከብራ ትኖራለች
ፈጣሪ አገራችንን ይባርክልን
 
ነሐሴ 12 /2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ምላሽ ይስጡ