የትራንስፖርት ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ አደረጉ
ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በደም ልገሳ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የሚኒስቴር መ/ቤቱ አመራርና ሠራተኛው ከአንድ ወር የደመወዝ ድጋፍ በተጨማሪ “ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል።
በአሁኑ ወቅት ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ከሚጠበቀውም በላይ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል::
የትራንስፖርት ዘርፉ ከመቼውም ጊዜ በተለየ በሥራ ቦታ የሚያከናወኑ ተግባራትን በተሻለ መንገድ ከመፈፀም በዘለለ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የ10ሩ ተጠሪ ተቋማት አመራር እና ሰራተኞች ከደመወዛቸው ከ57 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በዛሬውም ዕለትም የትራንስፖርት ሚኒስቴር አመራር እና ሰራተኞች ሀገርን የማዳን ዘመቻን የደም ልገሳ በማድረግ የተቀላቀሉ ሲሆን በግንባር ላሉ ጀግኖቻችን ደጀን መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል።