ከአዲስ አበባ ለመከላከያ ሠራዊት በሙያቸው ድጋፍ የሚሰጡ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ተሸኙ
ከራስ ቲያትር፣ ከሀገር ፍቅር ቲያትር፣ ከባህል አዳራሽ እና ከህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤቶች የተውጣጡ ባለሙያዎች ናቸው ወደ ግንባር የሚላኩት።
አርቲስቶቹ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ግቢ በአስተደዳሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።
ኢትዮጵያ ሳትወድ በግድ ጦርነት ውስጥ መግባቷን ያስታወሱት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተባበረ ክንድ በአንድነት በመቆም ሀገር ለማፈራረስ የተነሳውን የሽብር ቡድን ለመደምሰስ መላው ህዝብ መነሳቱንም ጠቅሰዋል።
ኪነ-ጥበብም ለድሉ ድርሻዋ ትልቅ ነው ያሉት ወይዘሮ አዳነች አርቲስቶቹ በተነሳሽነት ዘመቻውን ለመቀላቀል በመወሰናቸው አመስግነዋል።