You are currently viewing ‹‹መከላከያን በስንቅ፣ በሞራልና በትጥቅ በማጠናከር ሁላችንም የኢትዮጵያ ወታደር መሆናችንን ማስመስከር ይገባናል›› -ዶክተር ተመስገን ቡርቃ የክልሎች ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ

‹‹መከላከያን በስንቅ፣ በሞራልና በትጥቅ በማጠናከር ሁላችንም የኢትዮጵያ ወታደር መሆናችንን ማስመስከር ይገባናል›› -ዶክተር ተመስገን ቡርቃ የክልሎች ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ

  • Post comments:0 Comments
‹‹መከላከያን በስንቅ፣ በሞራልና በትጥቅ በማጠናከር ሁላችንም የኢትዮጵያ ወታደር መሆናችንን ማስመስከር ይገባናል››
-ዶክተር ተመስገን ቡርቃ የክልሎች ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ
 
‹‹መከላከያን በስንቅ፣ በሞራልና በትጥቅ በማጠናከር ሁላችንም የኢትዮጵያ ወታደር መሆናችንን ማስመስከር ይገባናል›› ሲሉ የክልሎች ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሰቢ ዶክተር ተመስገን ቡርቃ ገለጹ::
 
የኦሮሚያ ክልል ሴቶች አደራጃጀትና የሶማሌ ማህበረሰብ በዓይነትና በገንዘብ 24 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ::
 
የኦሮሚያ ክልል የሴቶች አደረጃጀት የ12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብርና የሶማሌ ማህበረሰብ የ11 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ለመከላከያ ሠራዊት አስረክበዋል::
 
የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር ተመስገን የኦሮሚያ ክልል የሴቶች አደራጃጀቶችና የሶማሌ ክልል ማህበረሰብ ለሠራዊቱ ወገንተኛ መሆናቸውን ለማሳየት ትናንት ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት፤ መከላከያን በስንቅ፣ በሞራልና በትጥቅ በማጠናከር ሁሉም የኢትዮጵያ ወታደር መሆኑን ማስመስከር ይኖርበታል::
 
ጠላቶቻችን በዙሪያችን እያሰፈሰፉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን ከመደገፍና ከማጠናከር ውጪ ምንም ዓይነት አማራጭ የለምንም ያሉት ዶክተር ተመስገን፣ ኢትዮጵያዊያን ሠራዊቱን ለመደገፍ በከፍተኛ ደረጃ እየተነቀናቁ ባሉበት ሰዓት ላይ እንገኛለን፤ ይህም ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል ብለዋል::
 
ህብረተሰቡ ልጆቹን ወደ ግንባር እንዲዘምቱ በመላክ ብቻ ሳይወሰን ሠራዊቱን በስንቅ ለመደገፍ ከፍተኛ ንቅናቄ እያደረገ መሆኑንም አመልክተዋል::

ምላሽ ይስጡ