ህጻናትን በውትድርና የሚጠቀመው አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈጸመበት የአፋር ክልል 107 ህጻናትን መግደሉን አልጀዚራ ዘገበ
የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወደ ጎን በማለት ህጻናትን ጭምር በማስታጠቅ የአፋር እና የአማራ ክልሎች ላይ ትንኮሳ እየፈጸመ ያለው አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል 107 ህጻናትን መግደሉን አልጀዚራ ዘግቧል።
አልጀዚራ በዘገባው ላይ እንዳለው፤ ይህ ቡድን ቃሊ ኩማ በተባለ የአፋር ክልል ውስጥ 240 ንጹሀንን ገድሏል። ከእነዚህ ሟቾች መካከልም 140ው ህጻናት ናቸው።
የአሸባሪው ታጣቂዎች ወደመንደሯ በመግባት በከባድ መሳሪያዎች በፈጸሙት ድብደባ ንጹሀኑን ገድለዋል ብሏል አልጀዚራ።
የአልጀዚራው ዘጋቢ ሀሰን አብደል ራዛቅ እንዳለው ህወሓት አሁንም በአፋር ክልል ላይ የሚያደርገውን ትንኮሳ ቀጥሎበታል።
አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል እየፈጸመ ባለው ትንኮሳ ከባድ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን፤ በዚህ በመበሳጨትም በግንባሩ ላይ ታጣቂዎቹን ሲመሩ የነበሩ አመራሮቹን ለመቀጣጫ በሚል አንገታቸውን በመቅላት ጭምር መግደሉ፤ የእርዳታ እህል የተከማቸበትን መጋዘን ማቃጠሉ አይዘነጋም።
የአሜሪከ ተራድኦ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሳማንታ ፓወር የህወሓት ታጣቂዎች ከያዟቸው የአማራ እና የአፋር አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ ቢሳስቡም፤ የአሸባሪው አፈቀላጤ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን በኩል ትንኮሳውን እንደማያቆሙ ከተባለው አካባቢም ለቀው እንደማይወጡ ማስታወቁ ይታወሳል።