You are currently viewing በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ፀጥታ ቢሮ አዘጋጅነት የሁለተኛ ዙር የመከላከያ ሰራዊት ምልመላን በማስመልከት በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ፀጥታ ቢሮ አዘጋጅነት የሁለተኛ ዙር የመከላከያ ሰራዊት ምልመላን በማስመልከት በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ

  • Post comments:0 Comments
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ፀጥታ ቢሮ አዘጋጅነት የሁለተኛ ዙር የመከላከያ ሰራዊት ምልመላን በማስመልከት በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ፀጥታ ቢሮ አዘጋጅነት የሁለተኛ ዙር የመከላከያ ሰራዊት ምልመላን በማስመልከት በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በመድረኩም ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ /ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ እና የክልሉ ሰላምና ፅጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ፣የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የፊት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ውይይቱ ላይ ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ በመገኘት መድረኩን የመሩት የክልሉ ፕሬዝደንት፣የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤትና የክልሉ ሰላማና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ የመጀመሪያ ዙር ምልመላ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን በቀጣይ ከክልሉ ከ13 ሺህ በላይ የሰራዊት አባላት ለመመልመል ዕቅድ የተያዘ ሲሆን በመድረኩ እንደተገለፀው ከዚህ ቀደም የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን የተገነባበት መንገድ የአንድ ወገን የበላይነት የነገሰበት መሆኑን ህብረ ብሔራዊ የሆነ መከላከያ ስርዓት ከመገንባት አኳያ ጉድለት እንደነበረና አሁን ይህንን የሚያስቀር ስራ እየተሰራ እንደሆነ በማንሳት በአሁኑ ወቅት ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በእኩልነት መከላከያን የሚቀላቀሉበት ዕድል መፈጠሩ ተንሰቷል። መድረኩም ላይ መግባባት ተፈጥሮ የዕለቱ ስብሰባ ተጠናቋል።

ምላሽ ይስጡ